0
#FastMereja I ኤፍ እና ቲ ኬብል አምራች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የኤሌትሪክ ኬብልን በማምረት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። ዛሬ ሕዳር 07/2017 ዓ.ም በስካይ ላይ ሆቴል በሰጡት መግለጫ ሰበታ በሚገኘው ኢንዱስትሪ ፓርክ ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኬብል፣ የመቆጣጠሪያ ገመድ እና ብጁ-የተሰራ የኬብል ምርቶች በማምረት ላይ ይገኛል እንደሚገኝ ነው የተገለፀው።
በተለይ አዲስ የተመረቱት የUSB አዳብተር ዘመኑን የዋጀ 3 ሶኬት 4 የUSB መሰኪያ እንዲሁም type c መሰኪያ ያለው መሆኑ በበርካቶች ተመራጭ ያደርጓል ተብሏል።
የኩባንያው ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ፎ እንደገለጹት ኤፍ ኤንድ ቲ የቻይና ኬብል አምራች ኩባንያ መሆኑን ገልፀው በኢትዮጵያ የኬብል ጥራት ችግርን የሚፈታ ዘመናዊ አሠራር ተግባራዊ በማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቀው በወር 50,000 አዳብተር እንደሚያመርቱ ገልጿል።
አሁን ላይ በሰንጋ ተራ እና በኡራኤል የኤሌክትሪክ መጨሻ ቦታዎ እየተሰራጨ ሲሆን በቅርቡ በሁሉም የክልል ከተሞች እንደሚገኝ ተነግሯል።





1 comment
እስቲ አምባሳደር አርጉኝ ምን አለበት 👐