banner

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የነዳጅ ግብዓትን በህገውጥ መንገድ በሚሸጡት ላይ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ገለፀ።

የነዳጅ መሸጫ ዋጋ በአለም አቀፍ ደረጃ መጨመሩን ተከትሎ እንደ ሀገር መንግስት የነዳጅን ዋጋ ለማረጋጋት ከፍተተኛ ወጪ በመመደብ የሚደረገውን ድጎማ ለታለመለተት አላማ ሳይውል በህገወጥ መንገድ ለሽያጭ በማቅረብ ህብረተሰቡ ለእንግልትና ለአላስፈላጊ ወጪ በመዳረግ ሰው ሰራሽ እጥረት እንዲፈጠር እየሰሩ ያሉ አካላትን ከድርጊታቸው ለማስቆም የክልሉ መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ግብረሃይል በማቋቋም ወደ ስራ ገብቷል።

የግብረሃይሉ ሰብሳቢ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ የምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በክልሉ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረትን በመፍጠር የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ እንዲቆይ እየሰሩ ያሉ አካላትን ከድርጊታቸው ለማስቆም የክልሉ መንግስት ቁርጠኛ አቋም የያዘ ሲሆን ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በግልፅ መወያየት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

ሀላፊው አክለውም ህገ-ወጥነትን የመከላከልና የህብረተሰቡን ጥቅም የማስቀደም ትልቅ ሀላፊነት ስላለብን በትኩረት በመስራት ሰው ሰራሽ እጥረትን በመፍጠር ህብረተሰቡን ላልተገባ እንግልትና አላስፈላጊ ወጪ የሚዳርጉትን የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች፣ ነዳጅ ወደ ማደያ ሳይገባ በኮንትሮባንድ አየር በአየር የሚሸጡ ባለሀብቶችን፣ ቤንዚልን በሀይላንድ የሚሸጡ ህገ-ወጦችን ሀላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው የህገ-ወጦች ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላትን በመለየት እርምጃ የመውሰድ ስራ አጠናክሮ በማስቀጠል ችግሩን በዘላቂነት የመቅረፍ ስራ ይሰራል ብለዋል

በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎትና ታሪፍ ዙሪያ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊዎች የጥናት ሰነድ ቀርቧል።

የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት መኩሪያ በክልሉ 60 ማደያዎች የሚገኝ ሲሆን 57ቱ ስራ ላይ ያሉ መሆናቸውን ገልፀው። እንደ ሀገር ያቅርቦት ችግር ያለ ቢሆንም የመጣውን ባግባቡ ከማሰራጨት አኳያ አየር በአየር ንግድ፣ የማደያ ቀጂዎች የስነ-ምግባር ችግር፣ የሚመለከታቸው አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ያለመወጣት ችግሮች በመኖራቸው የሚታየው ችግር እንዲስተዋል ምክንያት መሆኑን በሰነዱ አብራርተዋል።

ሃላፊዋ አክለውም የስብሰባው ተሳታፊዎችም በቤንዚል ስርጭት ላይ ስር የሰደደ ችግር መኖሩን አንስተው ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም በተቀናጀ ሁኔታ በቁርጠኝነት መስራት ከቻለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልፀዋል።

ህገ-ወጥ የቤንዚል ንግድን ለመቆጣጠር የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ በሆኑት በክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ የሚመራ በሁሉም ዞኖችና ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ የወጣውን እቅድ የሚያስፈፅሙ የተደራጀ ግብረ ሀይል ተቋቁሟል።





6 comments

Tsegaab Dawit November 20, 2024 - 5:08 pm

መፍትሄ ያመጣል ብለን እናምናለን ብርቱልን።

Reply
Dera Man Gessese November 20, 2024 - 5:12 pm

ስትራመዱ ቀስ እያላችሁ ሌላ ሀገር ድንበር እንዳትጥሱ።ሲጀመር ማነው በህገወጥ መንገድ ሚሸጠው?አታስቁን እስኪ

Reply
Getu Talu November 20, 2024 - 5:13 pm

ቆጮሰ

Reply
Kdemachew Kefyalew November 20, 2024 - 5:21 pm

ሻጭም እናተ ከማድያዎች ጋር በመመሳጠር ሕገወጥ የምትሉ እናተ

Reply
Asefa Kebede November 20, 2024 - 5:21 pm

” ማን ሆነና ”
ይህን ሁለት ቃል አረፍተነገር ልንለው እንችላለን ?🙄 እኔም ተጠይቀ እሺ 😌

Reply
Solomon Seyoum November 20, 2024 - 5:25 pm

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የነዳጅ ማደያና እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የነዳጅ ማደያ ችግር ባይኖርም በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ ከተማ በሁሉም ክ/ከተማ ምንም አይነት ከነዳጅ ማደያ ውስጥ የሚቀዳ ነዳጅ እንደሌለ “በማስመሰል” ሆን ተብሎ የክልሉን መንግስት እና ፌደራል መንግስቱን ከህብረተሰቡ “ለመነጣጠል” ሆን ተብሎ የታሰበ ሴራ ነው።

በክልሉ ከፌደራሉ መንግት በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት እየቀረበ ቢሆንም የነዳጅ ባለቤቶች በሚሰሩት የተለያዩ አሻጥር ምክንያት የነዳጅ ፍጆታ ለህብረተሰቡ በአግባቡ ሊደርስ አልቻለም።

ለከተማው የነዳጅ ችግር ምክንያት የሚሆኑት እራሳቸውን መንግስት አድርገው የሚያስቡ ባለሀብቶች ናቸው።

ሀዋሳ ከተማ ብቻ ሳይሆን እንደ ክልላችን ባለሃብቱ የነዳጅ ማደያ እየገነባ ያለው ለህብረተሰቡ አገልግሎትና የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት መሆን ይኖርበታል።

የክልሉ መንግት ልክ እንደቀድሞው ሁሉ ስርአት አልበኞችን እና ኮትሮባንዲስቶችን በቴክኖሎጂና በነቃ ህሊና ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ መስመር እንደሚያሲዝ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Reply

Leave a Comment