0
ኢትዮጵያ ውስጥ በግዙፍነቱ ወደር የለሹ የንግድ ስፍራ መርካቶ ሰኞ ሕዳር 9 ቀን 2017 ዓ. ም እና በማግስቱ ግብይትን በደረሰኝ ከማድረግ ጋር በተገናኘ ብዙ ሱቆች ተዘግተው አድማ ስለመደረጉ በወቅቱ ነጋዴዎች እና ሸማቾች ለዶቼ ቬለ ገልፀው ነበር።
ዛሬ ሐሙስ የገበያው እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል መሀል መርካቶ ውስጥ ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ የንግድ ተቋማቱ ተከፍተው መደበኛው ሞቅ ብሎ የሚታወቀው የግብይት ሁኔታ መጀመሩን ተመልክተናል። መንግሥት ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቀርብ ሰሞኑን ጥብቅ ክትትል ማድረግ መጀመሩን ማስታወቁን ተከትሎ በንግድ እንቅስቃሴው ላይ ውዥንብር ተስተውሎ ነበር።
ዘገባው የዶይቼ ቬለ ነው
