banner

ሞቢሊቲ ኢ ድርጅት ለሁለተኛ ጊዜ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለደንበኞቹ አስረከበ

በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለደንበኞቹ ያስረከብው ሞቢሊቲ ኢ ድርጅት ከድጋፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በተመቻቸው የብድር አማራጭ እና ዝቅተኛ የወለድ ፐርሰንት ተጠቅመው የደንበኝነት ውል የፈጸሙ ሀያ ደንበኞችን በዛሬው እለት ለሁለተኛ ግዜ በደማቅ ስነስረአት አስረከብዋል።

በዚህኛው ዙር የተረከቡት የመኪና አይነቶች BYD seagull, BYD E2, እና Song plus ሲሆኑ በዕለቱ ንግግር ያደርጉት የሰራ ሃላፊዎች ደንበኛ ተኮር በሆነ አገልግሎት በተጠናከረ መልኩ ከሀገሪቷ ካስቀመጠችው የታዳሽ ሀይል መጠቀም ስትራቴጂ ጋር በተጣጣማ ሁኔታ የኤሌክትሪክ መኪና ፍላጎትን ለማርካት እና አስደሳች የብድር አማራጮችን በማመቻቸት በሙሉ ሀይል እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በቀጣይ ከኤሌክትሪከ መኪና በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ሴክተሮች እና ኤሌክትሪክ ባይክ አማራጮችን ከድግፍ ማይክሮፋይናንስ ጋር በመተባበር ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ሲሆኑ ከድርጅቱ ጋር በመተባበር ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተገልጿል።





1 comment

Haile Beriso Boru November 23, 2024 - 3:12 pm

#JusticeForSalale
#JusticeForWollega
#JusticeforOromo

Reply

Leave a Comment