banner

#ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማዩን ዘጋው

አክአብ የሚባለው የእስራኤል ንጉስና ሚስቱ ኤልዛቤል እግዚአብሔርን ማምለክ ትተው ጣኦት ማምለክ ጀመሩ፤ አብያተ ክርስቲያናትን አፍርሰው አብያተ ጣኦታትን ሰሩ፤ ነብያት ካሕናትን አስፈጅተው 850 የጣኦት ካህናት ለራሳቸው አዘጋጁ፡፡ በዘመኑ የነበረው ነብዩ ቅዱስ ኤልያስ ተዉ እያለ ቢመክራቸው አልሰማ አሉት፡፡ እርሱም የሚያመልኩትን ጣኦት አቅሙን ይዩት ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማዩ ዝናብ እንዳይሰጥ ዘጋው፡፡

ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር፣ ስለ ሕገ እግዚአብሔር መከበር ምን ያህል ርቀት እንጓዛለን? ቢያንስ ቤተክርስቲያንን በአቅማችን ማገዝ ያለን ተነሳሽነት ምን ያህል ነው?

ይህ ለእግዚአብሔር ሕግ ቀናኢ ሆኖ የወሰደው እርምጃው እርሱንም ለስደት ዳርጎታል፡፡ በመጨረሻም ንጉሱ አክአብ ያስፈልገው ጀመር፡፡ በተገናኙ ወቅትም ነቢዩ ኤልያስ እስከመቼ በሁለት ልባችሁ ታነክሳላችሁ እግዚአብሔር አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ፤ ጣኦታችሁ ቤልም አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ በማለቱ የጣኦቱ ካህናትና እርሱ በየተራ መስዋዕት ሰው፡፡

በመጀመሪያ ነብያተ ሀሰቶቹ የጣኦታቸውን ስም እየተጠሩ ከሰማይ እሳት ወርዶ መስዋዕቱን ይበላላቸው ዘንድ ጠየቁ፤ መልስ ግን አላገኙም፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስም የሰርክ መስዋዕት ሰዓት ደረሰ ይበቃችኋል አላቸው፡፡ ለሙሴ በተሰጠው ሕግ መሰረትም የኦሪት መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቦ “የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ እን እከብርበታለሁ ብዬ ሳይሆን ለክብርህ ቀንቼ ነውና ስማኝ ሲል የሰዋበት መሬት ጋት ያህል እስኪቃጠል ድረስከሰማይ እሳት ወርዶ መስዋቱን በልቶታል፡፡ የሀሰት ነቢያትና የጣኦት ካሕናቱንም አስፈጅቷቸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጥቶ በመጸለይ ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ የዘጋውን ሰማይ እንዲከፈት ጸልዮ ዕለቱን ዝናብ አዝንቦላቸዋል፡፡ በዘመናችን ለቤተ ክርስቲያን ቀናኢ መሆናችንን ለማሳየት ሰማይን መለጎም አይጠበቅብንም እንደየአቅማችን ግን እጃችንን መዘርጋትና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማገዝ ይገባናል፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት ስር ለሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም እጃችንን እንዘርጋ፡፡

ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

Leave a Comment