banner

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ምስክር እንዲሆኑላቸዉ ያቀረቡት የአቶ ታዬ ደንደዓ ፤ ምስክሮቻቸዉ በችሎት አ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድን እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ምስክር እንዲሆኑላቸዉ ያቀረቡት የአቶ ታዬ ደንደዓ ፤ ምስክሮቻቸዉ በችሎት አልተገኙም ተባለ

በፍትህ ሚኒስቴር ተከሰው እስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ በቀጠሮያቸው መሰረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቢቀርቡም ለመከላከያ ምስክር የጠሯቸው ግን ሳይገኙ ቀርተዋል። “የጦር መሳሪያን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ይዘው ተገኝተዋል” በሚል የቀረበባቸው ሦስተኛውን የክስ ጭብጥ እንዲከላከሉ ከዚህ በፊት ብይን የተላለፈባቸው ታዬ፤ ጉዳዩን የሚያውቁ ብለው ከጠሩዋቸው 5 ተከላካይ ምስክሮች መካከል ሁለቱ ባለፈው ሰኞ ህዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም ቀርበው የምስክር ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

በእለቱ ቀርበው ምስክርነታቸውን የሰጡት የቀድሞ አለቃቸው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እና በፌዴራል ፖሊስ የአጠቃላይ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ነበሩ። ተከሳሹ ከጠሯቸው አምስት ተከላካይ ምስክሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲና ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ስም ከዚህ በፊት መጥቀሳቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ በተቀጠረው ችሎት ግን የቀረበ ተከላካይ መስክር አልነበረም።

ችሎቱ በዚህ ላይ ለተከሳሽ ማብራሪያ ሲሰጥ ምስክሮቹ ያልቀረቡት መጥሪያ ስላልደረሳቸው መሆኑንና ዛሬ ለታህሳስ 03 ቀን 2017 ዓ.ም ለተሰጠው ተለዋጭ ቀጠሮ ግን እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንደሚደርሳቸው አሳውቋል፡፡አቶ ታዬ ከታሰሩ በኋላ የሰብዓዊ መብት ጉዳዩ እንድመረመርላቸው የጠየቁት፤« ቤተሰቦቼ ከነበሩበት መኖሪያ ቤት ያለበቂ ጊዜ መሰጠት ተጣድፈው እንዲወጡ በመደረግ ደጅ መውደቃቸው፣ ለአራት ወራት ያለምንም የፍርድ ቤት ሂደት መታሰር እና ጠበቃ እንዳይቆምልኝ መከልከልን» በተመለከተ» ጥያቄ አንስተው፤ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተላከ ደብዳቤ እና ባለሙያ የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ እንደሚፈልግ ተነግሯቸዋል፡፡

በዚህ ላይ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ታዬ፤ ምርመራው መዘግየቱን ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የመጨረሻ ያለውን የ30 ቀናት ጊዜ ብቻ ለሰብዓዊው ተቋሙ ሰጥቷል። የቀድሞ ባለስልጣን አቶ ታዬ፤ ከዚህ በፊት በሰጡት የእምነት ክደት ቃል የጦር መሳሪያውን መያዛቸውን ሳይክዱ ክሱ የቀረበበትን አኳኳን ግን መሞገታቸው አይዘነጋም፡፡

ዘገባው የዶቼ ቬለ ነው

10 comments

Mekedes Mekdi November 26, 2024 - 4:06 pm

በቤተሰብ መሃል ጣልቃ አንገባም🙊🙊

Reply
እዮብ መኮንን November 26, 2024 - 4:09 pm

ታስሮ ነበር እዴ

Reply
Firafan Tuji Tuji November 26, 2024 - 4:10 pm

Free tayeee

Reply
Fitsum Maru November 26, 2024 - 4:11 pm

በፖሊስ ተይዘው መቅረባቸው ነው በቃ😴😴😴

Reply
Yosef Gebregziabher Gebru November 26, 2024 - 4:13 pm

በጣም ነው ዴ የታሰረው

Reply
Fikadu Moges November 26, 2024 - 4:17 pm

እንዲታሰር ያደረጉትን ያዘዙትን ሰዎች ምስክር ሁኑኝ ብሎ የጠየቀ የመጀመሪያው የአለማችን ድንቅ ሰው ታዬ ደንደዓ 😧👍

Reply
Novak Jokovich Cr November 26, 2024 - 4:18 pm

አታወዛግቡንዓ

Reply
Menber Tesfaye November 26, 2024 - 4:19 pm

Hulume seltan kentu mhonu masaya new
Batseboche ysazenalu enji

Reply
Yab Abirshi Yabu November 26, 2024 - 4:19 pm

ታማኝ ምስክሮች አደሉ 😂😂

Reply
Kibru Doge November 26, 2024 - 4:20 pm

እግሬ አዉጭኝ😳😳😳
ምን🤗

Reply

Leave a Comment