የኢትዮጵያ 10ኛው ክልል ሲዳማ መምህራን በግዴታ ለብልጽግና ፓርቲ ህንጻ ግንባታ እንድናዋጣ ጫና እየደረሰብን ነው ይላሉ።
በማዕከላዊ ዞን ደራራ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ለወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ህንጻ ግንባታ የአንድ ወር ደሞዛቸውን እንዲያዋጡ ተጠይቀው ያልተስማሙ መምህራን የጥቅምት ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ተናግረዋል።
ደሞዛቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ እና ያልፈረሙ 200 የሚሆኑ የደራራ ወረዳ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ መምህራን የጥቅምት ወር ደሞዝ አልተከፈላቸውም።
ለፓርቲ ጽ/ቤት ግንባታ መምህራንን ጨምሮ ከመንግሥት ሠራተኞች 16 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ የወጠነው ወረዳው “ግዴታ በልማት መሳተፍ አለባችሁ” በሚል ጫና እያሳደረብን ነው ብለዋል።
በ10 ወር ተቆርጦ የሚያልቅ የአንድ ወር ደሞዛቸውን እንዲያዋጡ የተጠየቁት መምህራኑ “እኛ እኮ ከምንሠራው ግብር ይቆረጥብናል፤ ይሄ ደግሞ ለልማት ነው የሚውለው. . .” በሚል ስብሰባ ላይ ማሳወቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
መምህራኑ ለተቃውሟቸው አቅም ካለመኖር ባለፈ፤ የብልጽግና ፓርቲ አባል አለመሆናቸውን እና ግዴታቸውም እንዳልሆነ በማስረገጥ ፊርማ አሰባስበው ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት አቤቱታ ማቅረባቸውን አንድ የሁለተኛ ደረጃ መምህር ተናግረዋል።
“የተባላችሁትን አድርጉ፤ ፈርሙ እና [ደሞዛችሁ] ይሰጣችኋል” የሚል ምላሽ ተሰጠን ያሉት መምህሩ፤ “እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት መፈረምን ነው” ሲሉ ያገለገሉበት ደሞዝ ‘በግዴታ መዋጮ’ እንደተያዘባቸው ገልጸዋል።
መንግሥት “አስገድዶ [ገንዘብ] እየወሰደ ነው” ያሉ ሌላ መምህር፤ ከአካባቢው አስተዳደር “የትም ብትሄዱ ዞራችሁ እኛ ጋር ነው የምትመጡት” የሚል ግልጽ ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል።
“ከተራቡ፤ ከተጠሙ መምጣታቸው አይቀርም ብለው እየዛቱ ነው” ያሉት ሌላ መምህር፤ የቤተሰብ አስተዳዳሪ የሆኑ መምህራን ተገደው እንደፈረሙም ተናግረዋል።
ለመዋጮው ፈቃደኛ ሆነው የፈረሙ መምህራን “ወደው ሳይሆን እስር እና ዛቻን፤ እንዲሁም ረሃብን በመፍራት ነው” ያሉት መመህሩ፤ “ሰቆቃ ውስጥ ነው ያለነው” ይላሉ።
“ተከራይ ነኝ፤ የቤት ኪራይ አልከፈልኩም። ሌሎች ወጪዎች አሉኝ፤ መሸፈን አልቻልኩም። ለምግብ ራሱ ሌላ ቦታ ከሚሠሩ ጓደኞቼ ተበድሬ ነው እየኖርኩ ያለሁት። ለመኖር በጣም እየተቸገርን ነው” ሲሉ አንድ መምህር ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።
“አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነን” ያሉ ሌላ ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህር “ሰው ሳይበላ አይሠራም” ብለዋል።
“መብቴን እየሠራሁ ስጠይቅ ቆይቼ ባለፈው ሳምንት ግን ሰው ሳይበላ አይሠራምና በጣም ስላቃተኝ [ትምህርት ቤት] መሄድም ስላልቻልኩ ሥራ አቁሜ ሌላ ቦታ ከምትኖር እህቴ ጋር ተጠግቼ ነው ያለሁት” ብለዋል።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

10 comments
Justice for Teachers
የሲዳማ ብቻ ነው የተራቡት 😄
ሀገራችን በምን አይነት ህፃን መሪሪሪ ነው የወደቀችው ግን???
በቅርቡ መንግስት አዲስአበባ ላይ ቀለብ ሲያቀርብ አላገጣችሁ። ደሞዝም ቢጨመርለት ከኑሮ ውድነቱ ሾልኮ ከሽሮ ወደ ስጋ ይሻገራል ማለት ዘበት ነው። ቅጥረኝነት በአጠቃላይ ዜሮ ስለሆነ ከቻሉ አርሰው ይብሉ።
It’s not fair 😴
የብልጽግና ሰወች ግን ህልማቸውን እየኖሩ ነው።
አብይ በቀን ለምግብ እና ለመጠጥ የሚያወጣውን ወጪ ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት። ይህ ኮተታም ድሃ፣ የመላጣ ልጅ ያንን ሁሉ ሚሊየን ብር ለመብል ሲያወጣ ከ90 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚበላውን አጥቶ ጥልቅ ርሃብ ውስጥ ባለበት ጊዜ መሆኑ በጣም ያንገበግበኛል።
Ere iyen miskin hizb atasekayut inante hod ader balesltanat ,hule sekoka mesmat selechen ,🥲
እውነት ለመናገር ችጋራም የድሀ ልጅ ስልጣን ላይ መውጣት የለበትም። ለካ አፄ ሀይለስላሴ የባላባት ልጆች ለምን እንደሚሾሙ አሁን ገባኝ🤔
ይሔ ነው የብልፅግና መጨረሻ ውጤት 😭
አንድ የመሆን ጊዜው አሁን ነው ሁሉም ሊነቃ ይገባል 🙄