banner

ኢያዋት ሽሪቫድሃናፕራብሃ ሩድ ቫን ኔስትሮይን ለመቅጠር ተቃርቧል

ሩድ ቫን ኔስተሮይ ከማን.ዩናይትድ ጋር ከተለያየ በሗላ በሌላ የፕሪምየር ሊግ ክለብ የዋና አሰልጣኝነት ሃላፊነት ለመረከብ ተቃርቧል::

የቀድሞው የማን.ዩናይትድ ዝነኛ የክለቦችን ፍላጎት እየሳበ ነው::

ሌስተር ሲቲ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሊሾመው እንደሆነ ዘገባዎች ወጥተዋል::

ቀበሮዎቹ በቼልሲ ከደረሰባቸው የ 2ለ1 ሽንፈት በሗላ አሰልጣኝስቲቭ ኩፐርን አሰናብተዋል እናም የክለቡ ባለቤት ኢያዋት ሽሪቫድሃናፕራብሃ (Aiyawatt Shrivadhannaprabha) በፍጥነት አሰልጣኝ ለመተካት ዝግጁ ናቸው::

በማን.ዩናይትድ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት ሽንፈትን ያላስተናገደው ጥሩ የሚባል ጊዜን ያሳለፈው እና በቅርቡ ከክለቡ ጋር የተለያየው ቫን ኔስተሮይ የሌስተር ምርጫ ሆኗል:: ቡድኑ ከብሬትፈርድ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ሃላፊነቱን እንደሚረከብ ይጠበቃል::

የ 48 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ ወደ ሃገሩ ተመልሷል:: ከሌሎች የአውሮፓ ክለቦች ጥያቄዎች ቀርበውለታል ነገር ግን ከሌስተር ጋር ያለውን ነገር ለመጠቅለል ውሉን ለመፈረም በፍጥነት ወደ እንግሊዝ እደሚመለስ ይጠበቃል::

በኦልድ ትራፎርድ ቆይታ ከማድረጉ አስቀድሞ በኤሪዲቪዚው ፒኤስቪን (PSV) ይዞ በጣም ጥሩ የውድድር ዘመን አሳልፏል:: ሁለት ዋንጫዎችን አሸንፏል ቡድኑን በመራባቸው 51 ጨዋታዎች ሽንፈት ያስተናገደው በስምንቱ ጨዋታዎች ብቻ ነበር::

በአዲሱ የውድድር ዘመን ከ 12 ጨዋታዎች በሗላ ስቲቭ ኩፐርን ከማሰናበት በሗላ ሌስተር ሌሎች አሰልጣኞችንም አጭቶ ነበር:: የቀድሞው የባየርን ሙኒክ አሰልጣኝ ኒኮ ኮቫች እና የአሁኑ የዌስት ብሮም አለቃ ካርሎስ ኮርበራንን::

አሁን ላይ ግን ቫን ኔስተሮይ ቁጥር አንድ ምርጫቸው ሆኗል:: የደቹ ሰው ነጻ ነው ደግሞም በፕሪምየር ሊግ ልምዱ የተሻለ ነው::

ቀበሮዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 16ተኛ ላይ ተቀምጧል ከወራጅ ቀጠናው በአንድ ነጥብ ብቻ ከፍ ብሎ:: ወደ መጣበት ቻምፒየንሺፕ በፍጥነት ተመልሶ መውረድን ለማስወገድ ጽኑ ፍላጎት አለው::

ሌስተር በቀጣይ አምስት የፕሪምየር ሊግ መርሃግብሮች ከብሬንትፈርድ ዌስትሃም ብራይተን ኒውካስል እና ዎልቭስ ጋር ይጫወታል::

[ሰላም ጎሳዬ (ሽሪቫድሃናፕራብሃ) 😉 ለፋስት መረጃ]

4 comments

አቡዘር አደም November 28, 2024 - 9:27 am

ሲሻር እንዳይቆጨው ሲሾም በደንብ ይብላ😁😁

Reply
Muluken Yonas Boltana November 28, 2024 - 9:27 am

ያነበባችሁ?

Reply
Meku Yemareyam Lij November 28, 2024 - 9:30 am

ስሙን እንደኔ ሳያነብ ያለፈ

Reply
Henok Tsehaye November 28, 2024 - 9:33 am

ሆነ እኮ already…..እንደስማቹ በጣም fast ናቹ🤣🤣🤣🤪

Reply

Leave a Comment