ታላቅ የንግስ በአል ጥሪ
“አቤቱ፣ ወደ አንተ በለመንሁ ጊዜ ጸሎቴን ስማኝ፣ ከጠላትም ፍርሃት ነፍሴን አድን” መዝ 64:1
ህዳር 21 ከታምረኛዋ እና ፈዋሿ የቃጥላ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አይቀርም!
ብዙዎች ከዚህ አለም ደዌ የተፈወሱባት፣ ከአጋንንት አስራት ነጻ የወጡባት፣ በምልጃዋ ጸጋና በረከት ያገኙባት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ንግስ በቃጥላ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ታዋቂ ሰባኪያን፣ ዘማሪያን ፣ ከሀገራችን እና ከመላው ዓለም የሚመጡ የእመቤታችን ወዳጆች በተገኙበት በድምቀት ይከበራል።
በፍቅር እና በአንድነት የሚያገለግሉ ካህናት አባቶች ያሉባት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የፈውስ አገልግሎቷ አሁንም ሳይቋረጥ ቀጥሏል፡፡ የቃጥላ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ለዓመታት መውለድ አትችሉም ተብለው ተስፋ የቆረጡ እናቶች እምባ ታብሶ ልጆቻቸውን አቅፈው የደስታ እምባ እያነቡ ምስክርነታቸውን የሰጡባት፤ በህክምናው የሞት ቀናቸው ተቆርጦ ሞታቸውን ሲጠባበቁ የነበሩ በእመቤታችን ጸበል ከደዌያቸው የተፈወሱባት፤ የእለት እንጀራ የሚያገኙበት ሥራ አጥተው ተስፋ ቆረጠው የነበሩ ሰዎች ህይወት በእመቤታችን ምልጃ ህይወታቸው የተቃናባት፤ ወዘተ ተዘርዝሮ የማያልቅ ፈውስ እና ተዓምራት የታየባት መሆኗን እንገልጻለን፡፡
በበዓለ ንግሷም የእመቤታችንን ጸበሏን ተጠምቀው፣ እምነቷን እና ቅብአ ቅዱሷን ተቀብተው የመከራ ቋጠሯቸው የተፈታላቸው፤ የፈተና እንቆቅልሻቸው የተመለሰላቸው ምእመናን ምስክርነት ይሰጣሉ።
ስለሆነም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ የእመቤታችን ወዳጆች፤ ምልጃዋ የደረሰላችሁ የእመቤታችን የአስራት ልጆች ህዳር 21ቀን ተገኝታችሁ የበረከቷ ተካፋይ እንድትሆኑ የደብራችን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
የቤተ ክርስቲያኗን የልማት ሥራዎች ለማገዝ፡-
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000249446975 ከውጭ አገር ለሚልኩ ስዊፍት ኮድ CBETETAA ፣ AYAT ADEBABAY ቅርንጫፍ
በአባይ ባንክ አካውንት ቁጥር 1641119375490017 ከውጭ አገር ለሚልኩ ስዊፍት ኮድ ABAYETAA ፣ BOLE ARABSA ቅርንጫፍ ይጠቀሙ
የቤተክርስቲያኗ ስልክ ቁጥሮች፡- 0944-44-48-06 ፣ 0944-44-48-26፣ 0944-44-48-36
