0
#FastMereja በካዛንቺስ ለበርካታ አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ፈንድቃ ባህል ማዕከል በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል አገልግሎት መስጠቱን ዛሬ ሕዳር 29/2017 ዓም በተሰጠ መግለጫ አስታውቋል።
የባህል ማዕከሉ መስራች መላኩ በላይ እንደገለፀው ሃያት ሪጀንሲ ሆቴል ፈንድቃን በሃያት ሪጀንሲ እንድንገነባ የፈቀዱ የሆቴሉን ስራ አስኪያጅ ከሪምን አመስግነው በካዛንቺስ ሲሰጥ የነበረው ሁሉም ፕሮግራም በሃያት ሪጀንሲ እንደሚሰጥ ገልጿል።
ከሰኞ እስከ እሁድ ምሽት ፕሮግራሞች የሚኖሩ ሲሆን መግቢያ ዋጋ በካዛንቺስ እንደነበረው 200 ብር መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መግቢያ በር በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በኩል እንደሆነም እውቁልኝ ብሏል።
ካዛንቺስ የነበረው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ቦታው እኛ እንድናለማ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቦታውን ከእኛ ሰጥቶኛል ለዚህ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እናመሰግናለን ሲል መላኩ በላይ ምስጋና አቅርቧል።




