banner

የቀድሞው አሰልጣኙ ላይ በ”ተኩስ” ምልክት ደስታውን የገለፀው የሀድያ ሆሳዕና ተጨዋች መነጋገሪያ ሆኗል ።

ዛሬ ሀድያ ሆሳዕናን ከሲዳማ ቡና ያገናኘው ጨዋታ በሀድያ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል ። ማራኪ ፏክክር በታየበት የምሽቱ ጨዋታ የሀድያ ሆሳዕናው አጥቂ እዮብ አለማየሁ ግብ አስቆጥሮ ያሳየው የደስታ አገላለፅ በስታዲየም የተገኘውን ተመልካች ቀልብ ስቧል ።

እዮብ ባለፈው የውድድር አመት በሀዋሳ ከተማ ጥሩ የውድድር ጊዜን ማሳለፏ ይታወሳል ።
ዘንድሮም ተጫዋቹን ለማስፈረም በርካታ ክለቦች ቢረባረቡም ማረፍያው በነብሮቹ ቤት ሀድያ ሆኗል ።

በ2013 ዓ.ም የአሁኑ የሲዳማ ቡና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው (ሞሪንሆ ) እና እዮብ በወላይታ ዲቻ ቤት አብረው ነበሩ ። በጊዜው ከቡድኑ በጉዳት ላይ ሆኖ ይቀነስ ቢባልም በደጋፊ ተፅእኖ በክለቡ አሳልፎ አጠናቋል ።

ከአሰልጣኙ ጋር ከ4 አመት በኋላ ተገናኝቶ ዛሬ በተቃራኒ የተጫወተው እዮብ ግብ ካስቆጠረ በኋላ ከ60 ሜትር በላይ ሮጦ የቀድሞ አሰልጣኙ የሚገኙበት የተቃራኒ ቡድን አባላት መቀመጫ ጋር በመምጣት ”በሩሜታ” ሳይሆን አነጣጥሮ በእጁ የተኩስ ምልክት አሳይቷል ።

ይህ ደግሞ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር የነበረውን ግንኙነት ምን ነበር አስብሏል ።

ሀድያ ሆሳዕና በፕሪሚየር ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ አምስት ተከታታይ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችሏል ። በ10 ጨዋታ 19 ነጥብ በመሰብሰብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።
ሲዳማ ተከታታይ 3 ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል ።

via: ሁሉ አዲስ

የደስታ አገላለፁን ቪድዮ ቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኙታል ።
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja

10 comments

Mekedes Mekdi December 9, 2024 - 8:21 pm

እና ኦነግ ሸኔ ብቻ ነው በተኩስ ደስታውን የሚገልፀው ያለው ማነው☺

Reply
Ttu Mamta Ttu Mamta December 9, 2024 - 8:23 pm

ኮቹ ተረፈ ግን 😜

Reply
Muhammed Ali Hassen December 9, 2024 - 8:23 pm

😂😂😂😂😂😂😂😂 “እረ ወይኔ

Reply
Bereket Elsae Zerfu December 9, 2024 - 8:24 pm

Eyob ገና ብዙ ብዙ ነገር ይጠብቃል
በርታ ጓዴ❤🤝
እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን❤

Reply
Freedom Onthewayof Fano December 9, 2024 - 8:25 pm

የማስተዋል ውጤት ነው። ትወና እንጅ እውነቱን አትጠብቁ! አብዮቱ ለትወና የሚሆኑትን ሰው መርጧልና!

Reply
Ef Rem December 9, 2024 - 8:26 pm

የሚያድግ ልጅን አትበድል ትል ነበር አያቴ። ቂም ይዞ ያድጋል

Reply
Lalisaa Dirribaa Urgaa December 9, 2024 - 8:28 pm

የኦነግ ታጣቂዎች መግባታቸውን ተከትሎ ደስታውን እየገለፀ ቢሆንስ 😂😎

Reply
ዮኒ ሳንጃው ከቤተል December 9, 2024 - 8:28 pm

🤷🏼‍♂️

Reply
Semu Arsenal Ethiopia December 9, 2024 - 8:32 pm

እና ፋኖ ብቻ ነው ተኩስ ባህላዊ ጭፈራ ነው ያለው

Reply
Heni Ethiopia Liverpool December 9, 2024 - 8:34 pm

የአዲስ አበባ የእግር ኳስ ምክትል ፕሬዝዳንታችን ምን ይሉ ይሆን😔

Reply

Leave a Comment