banner

ማንኛውም ሰው የፕላስቲክ የእቃ መያዣ ቀረጢት ይዞ ከተገኘ ከ5,000 እስከ 10,000 የሚያስቀጣው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወ

ማንኛውም ሰው የፕላስቲክ የእቃ መያዣ ቀረጢት ይዞ ከተገኘ ከ5,000 እስከ 10,000 የሚያስቀጣው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ረቂቅ አዋጁን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለውሃ መስኖ እና ቆላማ አካባቢ ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቶታል፡፡

ይህ በመላው hገሪቱ በ ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል የተባለው ረቂቅ አዋጅ 6 ክፍሎች ያሉት ሲሆን ከምንጩ ደረቅ ቆሻሻን መቀነስ መልሶ መጠቀም እና በአግባቡ ማስወገድ መሰረታዊ መርሆቹ ናቸው ተብሏል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የፕላስቲክ ምርት አምራቾች ላይ የሚከተሉትን ሀላፊነቶች ደንግጓል፡፡

በዚህም የፕላስቲክ ምርቱ የአገልግሎት ዘመኑ ሲያበቃ እንዲሰበሰብ ለዳግም ጥቅም ወይንም መልሶ ሁደት ላይ ሊውል የሚችልበትን ሥርዓት መፍጠር የፕላስቲክ ምርቱ የአገልግሎቱ ዘመን እንዳበቃ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ በአምራቹ ላይ ጥሏል፡፡

የደረቅ ቆሻሻን ስለመሰብሰብ በተመለከተም ከሚመለከተው አካል በሚሰጥ ፈቃድ ለጥሬ ምርትነት ካልሆነ በስተቀር ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትም የሚከለክል ነው፡፡

ረቂቅ አዋጁ የደረቅ ቆሻሻን አወጋገድን በተመለከተም ማንኛውም ሰው ለዚህ ዓላማ ተብሎ ከተለየ ቦታ ውጪ ደረቅ ቆሻሻን ማስወገድ እንደማይቻል ጠቁሟል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ ልዩ ልዩ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን በተመለከተም ማንኛውም ሰው ከ መኖሪያ ቤት ይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 20 ሜትር ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማፅዳት ሀላፊነት አለበት፡፡

ማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ወይንም የንግድ ተቋም ከይዞታው ድንበር አንስቶ ቢያንስ እስከ 50 ሜትር ባለው ርቀት ውስጥ ደረቅ ቆሻሻን የማጽዳት ሀላፊነት አለበት፡፡

ጠርሙስ፣ ጣሳ፣ የታሸገ ውሃ መያዣ ፕላስቲክን በተመለከተም ረቂቁ የምግብ፣ የመጠጥ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የመዋቢያ ምርቶችን በጠርሙስ፣ በጣሳም ወይም በፕላስቲክ መያዣ የሚያመርቱ፣ የሚያስመጡ፣ የሚያከፋፍሉ ሰዎች ጠርሙስ ወይንም የቆርቆሮ ጣሳ የአገልግሎት ዘመኑ እንዳበቃ መልሶ የሚወገድበትን ዘዴ የመዘርጋት ግዴታ አለበት ይላል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ የላስቲክ የእቃ መያዣዎችን ወደ ሀገር ማስገባት፣ ማምረት፣ መሸጥና ማከፋፈልን ይከለክላል፡፡

ይህን አድርጎ የተገኘም ከ50,000 ብር እስከ 200,000 ብር የገንዘብ ቅጣት እና ከ5 ዓመት ያልበለጠ ፅኑ እስራት ይጠብቀዋል ተብሏል ሲል ሸገር ሬዲዮ ነው የዘገበው።

10 comments

Helen Solomon December 10, 2024 - 4:47 pm

መጀመሪያ አማራጭ ማቅረብ አይቀድምም በምን ምክንያት ኪሳችሁ እንግባ አስመሰለባችሁ🙄

Reply
Esmael Abbaa Jabal December 10, 2024 - 4:47 pm

ሁሉም ቦርሳ ሊሸከም ነው

ሀዬ

Reply
Bini Bini December 10, 2024 - 4:50 pm

ወግ ወጉ ተይዞል ምን አለ ኑሮችንን የሚያሻሽል ረቂቅ አዋጅ ብታፀድቁ

Reply
Ones Love December 10, 2024 - 4:51 pm

በማዳበሪያስ🤣

Reply
አቡ አዩብ አደም ሙሳ December 10, 2024 - 4:55 pm

ፌስታል ቻው

Reply
አቡ ረያን ኢብን አብደላህ December 10, 2024 - 4:55 pm

ነገ ወርደው እነሱ የተራውን ማህበረሰብ ህይወት የማይኖሩት እየመሰላቸው የመጣውን ሁሉ እና ወረቀት ላይ የተፃፈውን ሁሉ መሬት ላይ ልሞክረው የሚልን የህዝብን ነበራዊ ሁኔታ ያለገናዘበን የካድሬ ሀሳብ ከማፅደቅ ቢቆጠቡ ነገን እነሰከኑ ይጠቅም ይሆናል።

Reply
Riyad Ebnu Muze December 10, 2024 - 4:55 pm

ሌላ የተሻለ ሀሰብ ጠፍቷዋቸዉ ነዉ መሰለኝ ህዝቤ በድሎት ላይ ነዉ ሚሉትስ ነገር ምቾቱ ህዝቡን እንዲረሱት አድርጓቸዋል ልበል!

Reply
የጣና ልጅ ነኝ ሀበሻ December 10, 2024 - 4:57 pm

መኪና ዉስጥ vomiting ፈቀዳችሁ በቃ

Reply
Teshe B Daba December 10, 2024 - 4:58 pm

ወደ ቀደምት ታርካችን እንመለስ….

ስልቻ(qanqalloo) አታቁም አይደል እናንተ 🥺

Reply
Amare Eyasie December 10, 2024 - 4:58 pm

ለማንቼስተር ዩናይትድና ለኦሮሚያ ፎስታል ይጭነቀው ንጅ ማን ይይዛል፣ስራ አጥታችሁ ሃገሪቱን የምታሳድጉበት መላ ቅጡ ጥፍት አለባችሁ አ😔

Reply

Leave a Comment