0
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ተመን ይፋ አድርጓል፡፡
ግብር ስወራን ለመከላከል በሚል ለንግድ ዘርፎቹ ስራ ላይ የዋለው የሰራተኛ ደመወዝ እና የሰራተኛ ቁጥር ተመን የህጋዊነት ጥያቄ አስነስቷል፡፡
አነስተኛ የደመወዝ ወለል በህግ ባልፀደቀበት ሁኔታ ‘’ዝቅተኛ መክፈል የምትችሉት ደመወዝ 5,000 ብር ነው ብሎ በመወሰን ግብር መሰብሰብ ህገ-ወጥ አሰራር ነው’’ ተብሏል፡፡
ዘገባው የሸገር ኤፍ ኤም ነው።
10 comments
በበተን ስልክ ነው እንዴ ፎቶ ያነሳችሁት🙄
ወይኔ በላቸው ናማ መነጸሬን አምጣልኝ
ግብር ለማስከፈል እንድመቻቸው ነው😃😃😃
ስጋ ቆራጭ??😂😂 ደስ ይላል
ምንም አልገባኝም
በኢትዮጵያ ውስጥ ዝቅተኛ ደሞዝ ተመን በአዋጅ መፅደቅ አለበት ጎረቤት ሐገሮች እንኳን ለምሳሌ ኬንያን ብና ለአንድ ሰው የሚከፈለው ዝቅተኛ የሚባለው ደሞዝ ወቅቱን ያገናዘበና የቤትክራይ: የምግብና መጠጥ: አልባሳትን በመጠኑም ቢሆን የሚሸፍን ደሞዝ መሆን አለበት ብለው ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን በአዋጅ አፅድቀዋል ከዛበታች ለሰራተኛው የከፈለ አሰሪ በሕግ ተጠያቂ ይሆናል።
ስራ አጥነትን የሚያባብስ ተግባር ነው።
የብሮው ሰራተኛ ራሱ ይሀን ያክል ደሞዝ ያላገኙ ብዙ ናቸው
ወይ ግራ መጋባት
አሰሪው በገቢው ልክ ነው ሚከፍላቸው እንጂ ገቢዎች የእያንዳንዱን ሆቴል የቀን ገቢን ሳያውቁ በዝህ ልክ መጨማለቅ ተገቢ አይደለም።
ወይስ…ለሆቴሎችም ከስቴመር ያሰባስባሉ?። ያን ያክል ደሞዝ የሚከፍሉበትን ወጪ መሸፈኛ በጀትም ይመድባሉ?😏