banner

መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ ፀደቀ።

#FastMereja
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

የጸደቁ አጀንዳዎች:-

1ኛ. የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

2ኛ. በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በመወያየት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

3ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በጥልቅ በመወያየት በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ

4ኛ. በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ

5ኛ. ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡


10 comments

Māštěwāl Ķàššayě December 13, 2024 - 5:33 pm

እስከ ምሽት 3:30 ውጪ የቆየ ሰው ወደ ቤቱ ይገባል እንዴ🤔

Reply
Zedo Hussen December 13, 2024 - 5:34 pm

ጀግና 👌👌👌👌

Reply
Zele Man December 13, 2024 - 5:35 pm

መንግስት ሀንግ ከሚሰሩት ጋር በኮሚሽን ተደራደረ እንዴ🤔

Reply
Sembetu Adalo December 13, 2024 - 5:35 pm

ሔርማን ነኝ ከቦሌ😂

Reply
የቼ ማን December 13, 2024 - 5:36 pm

ያዝ እንግዲ

Reply
Omerta Omerta December 13, 2024 - 5:36 pm

5ኛ የሀይል ብክነት 😁😁😁😁

Reply
Bayu Bayu December 13, 2024 - 5:37 pm

litazerifun

Reply
Eskindir Dagnew December 13, 2024 - 5:38 pm

መንገድ ዳር የምትሉት ምን ቤት አለና ነው

Reply
Mehabesha Mohammad December 13, 2024 - 5:39 pm

Tewat Sint Seat Enkifet

Reply
Jemal Seid December 13, 2024 - 5:40 pm

እስከ 3:30 አገልግሎት የሚሰጠን አላጣንም መግዛዉንም ብታስቡበት መልካም ነበር

Reply

Leave a Comment