banner

የቅድስት ስላሴ ታቦተ ህግ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል ገባለ

#Ethiopia I የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ወደ ፍፃሜ በመድረሱ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ታቦት ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ ለመመለስ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለፀ።

የካቴድራል የዕድሳት እና የጥገና ስራ ከተጀመረ 773 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን በየጊዜው በገጠመው የሲሚንቶ ችግር እና ሌሎችም ሁነቶች ምክንያት ተጨማሪ 225 ቀናት መውሰዱን ተጠቁሟል።

የህንጻውን ግንባታ ለሚያከናውነው ኮንትራክተር እስካሁን ድረስ ከ124 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ እንደተከፈለው የተነገረ ሲሆን ቀሪ ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ ህዝበ ክርስቲያኑ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ተደርጓል።

የቤተክርስቲያን እድሳት ሂደት 95 በመቶ የደረሰ ሲሆን ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በመላው ዓለም የሚካሄድ የቀጥታ ስርጭት የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት በየተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚካሄድ ሲሆን ታህሳስ 27/2017 ዓም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል የምስጋና መርሐ ግብር ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።





3 comments

Natnael Habtamu December 18, 2024 - 9:11 am

ገባለን ወደ ተባለ ቀይረው

Reply
Himanot Alemu December 18, 2024 - 9:11 am

እግዚአብሔር ይመስገን ቤቱን ይሰራል

Reply
ሰሊ ደበበ December 18, 2024 - 9:17 am

የዛ ሰው ይበለን🙏

Reply

Leave a Comment