0
#FastMereja I አማራ ባንክ ኪዊአር፣ ከባ ስማርት ፖስ፣ አባ ስኩል ፔይ እና አባ ሞባይል ባንኪንግ በዛሬው እለት አስተዋወቀ።
መተግበሪያዉ ተገልጋዮች ማንኛውንም አይነት ግብይት ሲፈጽሙ የእጅ ስልካቸውን ብቻ ተጠቅመው በግብይት ማዕከሉ የሚገኘውን የነጋዴውን QR code ቅኝት በማድረግ ያለ ጥሬ ገንዘብ ከማንኛውም የባንክ ሂሳባቸው በቀላሉ ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት እንደሆነ የባንኩ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ገልጿል።
በአባ ስኩል ፔይ ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ክፍያ መከታተል እና መቆጣጠር የሚችሉ ሲሆን ከመረጡት ባንክ ወይም እንደቴሌ ብር ካሉ የዋሌት ሂሳባቸውን በጊዜው መፈጸም የሚችሉበትን አማራጭ አማቅረቡም ተሰምቷል።
አማራ ባንክ በዲጂታል ዘረፉ ሁሉም ባለበት ለመድረስ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ባንኩ ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ሳፋሪ ኮም፣ ከብሔራዊ ስዊች፣ ከፋይናንስ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ ክፍያ አመቻቾችና ገቢዎች ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑ አስታዉቆል።



1 comment
ምንድነው ባንኩ አባ ‘አባ ‘ ማለት አበዛ?? ባንኩ ወደ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሊቀየር ነው እንዴ? 😃