banner

‎የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በከተማዋ ያለውን ሰላምና የሀይማኖት መቻቻል እኩልነትን የሚያሳይ እንደሆነ ተገለፀ

‎
‎የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊና አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በዓመት ሁለት ጊዜ በክልሉ ርዕሰ መዲና ሀዋሳ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል።
‎
‎በዚህ በዓል ላይ ለመታደም ከሀገር ውስጥና ከባህር ማዶ የሚመጡ ምዕመናንና እንግዶች የሀዋሳን ሰላማዊትና ለመሰል ሀይማኖታዊና ክብረ በዓላት ብሎም ለቱሪዝም ምቹ መሆኗን የሚጠቁም ነው ብለዋል።
‎
‎ዛሬ የተከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ያለ ምንም ኮሽታ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ባማረ መልኩ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሀይሉ እና ምዕመኑ በጋራ በመሆን ያበረከተው ታላቅ ስራ ስለመሆኑም ነው የቢሮ ሀላፊው የገለፁት።
‎
‎የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ በበዓሉ ላይ በመገኘት መልዕክታቸውን በማስተላለፍ ለምዕመኑ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
‎
‎ከንቲባው በመልዕክታቸው አባቶች የሰጡንን ታላቅ ሀገር በጋራ በመሆንን እና በመቻቻል ከዳር ለማድረስ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
‎
‎ውቧ ከተማችን ሀዋሳ ይህን በዓል በታላቅ ጉጉት ከምጠብቀው አንዱ ሀይማኖታዊ ክብረ በዓል ውስጥ ይጠቀሳል ሲሉም ነው የገለፁት።
‎
‎ለዚህ የከተማዋ ፍላጎት ውስጥ አንዱ የሆነው ከተማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን የሀይማኖታዊ ክብረ በዓላት አከባበርን ጨምሮ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ፍላጎትን አጉልተን የምናሳይበት ልዩ ቀን በመሆኑ ነው ሲሉም ተናግረዋል ከንቲባው።
‎
‎በዚህም እንግዶቻችን ከተለያዩ አካባቢዎች እና ክፍላተ አለማት በመምጣት በዚህ ቀን በከተማችን በዓሉን በልዩ ድባብ እያከበሩት እንደሚገኝ ማሳያ ነው ብለዋል።
‎
‎የበዓሉ ታዳሚያንም በዚህ ቀን በከተማችን ሲገኙ ከሚያገኙት መንፈሳዊ በረከት ባሻገር ስለ ከተማችን አምባሳደር በመሆን ጭምር የበኩላቸውን እንዲወጡ የበኩላችንን ጥረት አድርገናል።
‎
‎በዚህም ስኬታማ የሆነች ውብ ከተማን መገንባት ችለናል ብለዋል።
‎
‎ለዚህ ደግሞ ሁላችንም የከተማዋ ከንቲባ ነን በሚል መንፈስና ታላቅ ተጋድሎ የበኩላችንን እንድንወጣ ይገባል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
‎
‎የቅዱስ ገብርኤል የታህሳስ የንግስ በዓል በሀዋሳ ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት ምዕመኑ መንፈሳዊ በረከቱን በመቀበል በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።
‎





2 comments

Hailemariam Zewdu December 28, 2024 - 1:11 pm

ታቦት አጠግብ ምዕመን (ካህን ያልሆን ) መቀመጡ ከስርዓ ዉጭ ነዉ።

Reply
Bini Obamahairstayle December 28, 2024 - 1:12 pm

🥰🥰🥰🥰

Reply

Leave a Comment