የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በመገኘት ጉብኝት አደረጉ።
የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ መቃሪዮስ በሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በመገኘት የተጀመሩ ልማታዊ ስራዎችን በመጎብኘት እና ቡራኬ በመስጠት አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል የአንድነት ገዳም በስሩ ከዘጠና በላይ አባት እና እናት መነኮሳት በአንድነት የሚኖሩበት ቅዱስ ስፍራ ሲሆን ገዳሙ በመብል እጥረት እና በባዕት አለመኖር እንዲሁም ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች ገዳማውያኑ በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆኑን በ2016 ዓ.ም በማኅበረ መነኮሳቱ በተደገ የይድረሱልን ጥሪ ሁላችንም የምናስታውሰው ልብን የሚነካ እና ከአዕምሮ የማይጠፋ ክስተት ነበር።
በዚህ ጥሪ መሰረት በከፍተኛ ደረጃ በተደረገ የማኅበራዊ ዘመቻ ንቅናቄ መሰረት በዋናነት ባለ አስራ ስምንት ክፍል የእናቶች ባዕት የተገነባ መሆኑን ገዳማውያኑ አሳውቀዋል።
በመሆኑም ብፁዕነታቸው እነዚህን የእናቶች ማረፊያ በመባረክ እና በመጎብኘት በእናቶች በኩል የተከናወኑ ተግባራትን አድንቀዋል።
ብፁዕነታቸው በዚህ መንፈሳዊ ሥራ ላይ የማኅበራዊ ትስስር ድረገፆችን በመጠቀም ሱታፌ ያደረጉ ምዕመናን ያመሰገኑ ሲሆን እገዛችሁ ለፍሬ በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አያይዘውም በማስተባበር ሂደት ታላቅ እንቅስቃሴ ያደረጉ የተለያዮ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ባለቤት ለሆኑ አካላት እና ተቋማት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
ብፁዕነታቸው እንዳሉት የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የአባቶች ባዕት ያለበት ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ አባቶችን የማደራጀት እና የማቋቋም ስራ እንዲሁ አፋጣኝ እርብርብ የሚሻ ጉዳይ ነው ብለዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ ማኅበረ መነኮሳትን ለማጽናት፣ በዘለቄታዊነት ካሉበት ችግር ለማላቀቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እገዛችሁ ያስፈልገናልና የድጋፍ እጃችሁ አይታጠፍ፣ ልገሳችሁን አጠናክራችሁ ልትቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
አክለውም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በችግር ላይ የሚገኙ ገዳማትን እና እድባራትን መርዳት የእያንዳንዱ ክርስቲያን ግዴታ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ገዳማውያኑ ለሚያቀርቡት የድጋፍ ጥሪ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን የቀድሞውን እርብርብ በአባቶች ገዳም የባዕት ግንባታ ላይም በገንዘብ፣በዕውቀት፣በጉልበት በመርዳት የበኩላችንን ሀላፊነት እንወጣ ዘንድ አባታዊ መልዕክታቸውን በጥብቅ አሳስበዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ድጋፍ ለማድረግ ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም:-
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ:-1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ:-141029444
ለማንኛውም አይነት መረጃ:-
በ09 18 07 79 57 ወይም 09 38 64 44 44 መደወል የምትችሉ መሆኑን ያሳዉቁ ሲሆን ጅማሬያችን ታናሽ ቢሆንም ፍፃሜያችን ታላቅ ነው እና የጀመርነውን እንፈፅም ዘንድ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሆኑት በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ አባታዊ ፀሎት እና ቡራኬ የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል።
፳፫/፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ጎንደር ኢትዮጵያ




