banner

በአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከሰተ

2 comments

Gezehagn Hadaro January 3, 2025 - 8:47 am

#ይድረስ
➣ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ
➣ለብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት
➣ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ቦርድ
➣ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

ጉዳዩ:- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን #በዱራሜ-ዳምቦያ-አንጋጫ-ዋቶ-ሀላባ መንገድ እየደረሰ ያለውን በደል ስለማሳወቅና ዋና ተቋራጩ በአስቸኳይ እንዲቀየርልን ስለመጠየቅ ይሆናል።

ታህሳስ/2013 ዓ.ም የመሠረት ድንጋዩ የተጣለው የዱራሜ-ዳምቦያ-አንጋጫ-ዋቶ-ሀላባ የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ታህሳስ/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል በሚል የመሠረተ ድንጋዩ የተጣለ ሲሆን የማህበረሰቡን እና የአከባቢውን ሕዝብ የዘመናት ችግር እንዲፈታ በለውጡ መንግስታችን ትልቅ ትኩረት ተጥሎበት የተጀመረ መንገድ ነበር።

መንገዱን በዋና ተቋራጭነት እንዲመራ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የተሰጠ ቢሆንም ባለፋት አራት አመታት የተግባር አፈጻጸሙ ሲገመገም የተቀናጀ የስራ እና የእቅድ አፈጻጸም ካለመኖሩ የተነሳ እጅግ ዝቅታኛ ከመሆኑም በላይ የአከባቢውን ሕዝብ ለከፍተኛ እንግልት እንዲሁም ለአላስፈላጊ አደጋ በመዳረግ ከተሰጠው የኮንትራት እድሜ በላይ ከፍተኛ ኪሳራ በሁሉም መስክ እንዲዳረግ ያደረገ ነው።

በመንግስት እና በአከባቢው ሕዝብ ብሎም ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በጥራት እንዲሁም በፍጥነት በማጠናቀቅ ለአህጉራችን አፍሪካ አራዓያ በመሆን በሚታወቀው የብልጽግና ፓርቲ መሐል የፕሮጀክቱ አፈጻጸም በእጅጉ አዝጋሚ እንዲሁም ተስፋ የማይሰጥ ከመሆኑ አንጻር ከፍተኛ ቅሬታ በተቋራጩ (በኢኮስኮ) የመንገድ አሰራር የተነሳ እየተፈጠረ ይገኛል።

በቅርቡ የመንገዱ አማካሪ ድርጅት ስለ መንገዱ አጠቃላይ አሰራር ለኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ባስገባው dissatisfaction letter የመንገዱ ተቋራጭ በአስቸኳይ እንዲቀየር ብሎም ተስፋ ሰጪ ያልሆነ የተግባር አፈጻጸም ክፍተት በተቋራጩ ላይ እንደሚታይ አረጋግጧል።

ስለዚህም ከላይ የተጠቀሳችሁ አካላት የአከባቢውን ሕዝብ ከፍተኛ እንግልት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢኮስኮን ተቋራጭ ነገ ዛሬ ሳትሉ በአስቸኳይ ከመንገዱ በማስወገድ ሌላ የተሻለ ተቋራጭ ወደ መንገዱ በመተካት መንገዱ በአጭር ጊዜ በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ እንዲደረግ እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በመንገዱ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል በአግባቡ የምታውቁ ስለሆነ አማካሪ ድርጅቱ በሰጣችሁ አቅጣጫ እርምጃ በመውሰድ መንገዱ በተሻለ ተቋራጭ እንዲጠናቀቅ እንድታደርጉ ሐገራዊ እና ሕዝባዊ ሐላፊነታቹን እንድትወጡ በድጋሚ እንጠይቃለን።

Reply
John Mikii January 3, 2025 - 8:47 am

እሰይ እንኳን ደስ አላቹ ፈጣሪ ይመስገን ከማለት ውጭ ምን ይባላል መሬቱ ተነፈሰ መንቀጥቀጡ ይቆማል ማለት ነው ሲል የብልፅግና ፓርቲ አስታወቀ

Reply

Leave a Comment