banner

አለምፍሬ ፒንክሃውስ ካንሠር ፋውንዴሽን መላው ኢትዮጵያዊ ከድርጅቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቀረበ

#FastMereja I አለምፍሬ ፒንክሃውስ ካንሠር ፋውንዴሽን በዶክተር ፍሬህይወት ዴርሶን በአሜሪካ አትላንታ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በካንስር ህመም ላይ ቅድመ መከላከል የግንዛቤ መስጫ ጀምሮ በአዲስ አበባ እና በጎንደር ከ8000 በላይ የካንሰር ታማሚዎችን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገ የሚገኝ ድርጅት ነው።

የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ዛሬ ታህሳስ 25/2017 ዓም በጊዮን ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጡ ሲሆን አለም ፍሬ ፒንክ ሀውስ ካንሰር ፋውንዴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ በጡት ካንሰር ተጠቂ ሆነው የሚገኙ የገንዘብ እና የግብዓት ውስንነት ያለባቸውን ኢትዮጵያውያን ታማሚዎችን ለመርዳት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት እንደሆነ ተገልጿል።

የካንሰር ታማሚዎች ጤና የእርሶም የእኔም የሁላችንም ጉዳይ ነው የሚለው ድርጅቹ ኢትዮጵያዊያን እጃቸውን እንዲዘረጉ ጠይቋል።

አሁን እየሰራካለው በተጨማሪ በቀጣይ በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት የተለያዩ እቅዶችን ነድፎ ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ተዋናይ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ላቀው የአለምፍሬ ፒንክሃውስ ፋውንዴሽን አምባሳደር በመግለጫው ላይ ተገኝቶ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ድርጅቱን እንዲደግፍ መልዕክት አስተላፏል።





Leave a Comment