0
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ፖል ፎቶ፣ ቬሎ፣ ሜካፕ ባለቤት ወጣት ጳውሎስ ጎይቶም እንዳለው ድርጅቱ ከሚያገኘው ገቢ ላይ በቀን ቢያንስ 100 ሰው በልቶ እንዲያድር ማድረግ እንደሆነ ገልጿል። ወገኔ ሳይበላ አልበላም ለ3 ወራት በ100 ሰዎች የሚቀጥል ሲሆን ከሶስት ወራት በኋላ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ በርካታ ሰዎችን ለመመገብ እንደታቀደ ጳውሎስ ተናግሯል።
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 10 ኪሎ ዱቄት እና 5 ሊትር ዘይት ለ100 ሰዎች ድጋፍ ተደርጓል።
ፖል ፎቶ፣ ቬሎ፣ ሜካፕ ከ2 አመት በፊት የተመሰረተ ሲሆን በሀገራችን የመጀመሪያው የሰርግ ፓኬጅ አቅራቢ ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለ86 ቋሚ ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሯል።





2 comments
ስህራይ መልካም ነው ግን ለካሜራ አታርገው
ወንድሜ ተባረክ