banner

አሚጎስ በገና ዋዜማ 16 አባላቱን የመኪና ባለቤት አደረገ።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የግል ህብረት ስራ ማህበር ከበላይ አብ ሞተርስ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ለ16 አባላቱ በዛሬው እለት ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ሳሪስ በሚገኘው በላይ አብ ሞተርስ በመገኘት መኪናቸውን አስረክበዋል።
መኪና አስረክቧል።

ማህበሩ ቅድመ ሁኔታውን ላሟሉ አባላቱ የመኪና ርክክብ ያደረገ ሲሆን እነዚህ አባላት አምስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በ30% ቅድመ ክፍያ የመኪና ባለቤት ማድረጉን በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።

ከማህበሩ መኪናቸውን የተረከቡ ደንበኞች ከዚህ በፊት በሌላ ድርጅት ገንዘባቸውን ከፍለው የተጓተተባቸው የነበሩ ሲሆን ከአሚጎስ በገቡት ስምምነት በአምስት ወራት ውስጥ መኪናቸውን መረከባቸውን ተናግረዋል።

ከተመሰረተ 12 አመት ያስቆጠረው አሚጎስ እስካሁን ድረስ ከ1ሺህ ለሚበልጡ ደንበኞች የብድር አገልግሎት የሰጠ ሲሆን በእስካሁን ቆይታው ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለደንበኞቹ በብድር መልክ ማቅረቡንም አስታውቋል።





1 comment

𝚗𝚊𝚏𝚊𝚔𝚒𝚠𝚊 January 6, 2025 - 11:19 am

እንኳዕ አደረሳችሁ😔👐

Reply

Leave a Comment