banner

እነሆ እንዲህ ያለ የቂርቆስ ወጣቶችን በፍቅር አንድ አድርጎ ያስተባበረ የስፖርት ውድድር በጨርቆስ ሰፈር ውስጥ ከተደረገ ድፍን

እነሆ እንዲህ ያለ የቂርቆስ ወጣቶችን በፍቅር አንድ አድርጎ ያስተባበረ የስፖርት ውድድር በጨርቆስ ሰፈር ውስጥ ከተደረገ ድፍን ሁለት አስርት አመታት ተቆጠሩ። 38 ሜዳ አስር ቀበሌ ሜዳ አለፍ ሲልም 34 ሜዳ 35 ሜዳ እንዲህ ያለ ውድድር ካስተናገዱ አመታት አልፈዋል ።

ታላላቆቻችን ሲጫወቱ በልጅነት ልብስ ይዘን የምናየው ጨዋታ በዚህ አመት ተደግሟል ምንም እንኳን በተለያዩ ምክንያቶች የአከባቢው ወጣቶች ቢርቁም ሀገር ውስጥ ያሉት ከመንደር ርቀው ያሉትን መጥተው በመታደም ወንድማማችነት ገልጸዋል ።

ላለፋት ወራት ሲካሄድ የነበረው ጨርቆስ ካፕ ውድድር በትናንትናው ዕለት የክብር እንግዶች በተገኙበት ፍጻሜውን አግኝቷል ።

በዕለቱም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስፖርት ጽ/ቤት አቶ ጠብቀው አመሸ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሸናፊ ግርማ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና የቅዱስ ጊዮርጊስ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ምንያህል ተሾመ የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡናና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዳዊት እስጢፋኖስ የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾችና አሰልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ የኢቢኤስ የስፖርት አዘጋጆች ጋዜጠኛ ምስጋና መብራቱ እና ጋዜጠኛ ይድነቃቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወጌሻ ጋሽ ይስሐቅ ሽፈራው የቀድሞ የሴቶች አሰልጣኝ በለጥሽ ገ/ማርያም እንዲሁም በቀድሞ በተለያዩ ክለቦች ተጫውተው ያለፉ ሌጀንድ ተጫዋቾች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

ይኸ ውድድር ብዙ ነገር አስተምሮናል ከውድድርነቱ ባሻገር ሁላችንም የጨርቆስ ልጆች በሕብረት ለወንድማማችነት ቆመናል ። ለኳ ወጣቱ የሚያስተባብረው ነው እንጂ የሚፈልገው ውሎውን ኳስ ሜዳ ማድረግ ነው። እንደ ቀድሞ ስመ ጥር የክለብ ተጫዋቾች በክለብ ደረጃ መጫወት ነው ፍላጎቱ እንደ ቀዌ ረድኤት ሴካ የማነ ቴዲ ዮናስ መኩሪያ አያልነህ ክብረት ግዝቼ ደጎል ቀስቴ ወዘተ የመሳሰሉት ታዳጊ ተጫዋቾች ማፍራት ነው የጨርቆስ ካፕ ዋና ዓላማው።

ወንድማማች የሆኑት የማርገጃ እና የቢሜዳ ልጆች በወርሃ የካቲት ትምህርት ቤት ቅጽር ጊቢ ለፍጻሜ ቀርበው ከብርቱ ፉክክር ጋር ጨዋታው በአቻ በመጠናቀቁ በመለያ ምት በማሸነፍ የማርገጃ የጤና ቡድን 2017 የጨርቆስ ካፕ ዋንጫ አንስተዋል ።
ቸር ይቆየን
ቢኒ ዘቂርቆስ





Leave a Comment