banner

በአጋሮ ከተማ ፈለገ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የፈለገ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የቤተ አብርሃም ክፍል ወጣቶች በከተማዋ

በአጋሮ ከተማ ፈለገ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የፈለገ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት የቤተ አብርሃም ክፍል ወጣቶች በከተማዋ ለሚገኙ ደጋፊና ጧሪ የሌላቸውን ከ300 በላይ ለሚሆኑ ሕፃናት ፣ ወጣቶችና አዛውንቶችን በመሰብሰብ ፀጉራቸውን በመላጨት ፣ ገላቸውን የማጠብ ፣ ከተለያዩ ወገኖች ያሰባሰቡትን ልብስ በመለገስና ምሳ በማጋራት የገናን በዓል በመልካም ተግባር እያሳለፉ ይገኛሉ።

የቤተ አብርሀም ክፍል ወጣቶች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖችን በመለየት ከተለያዩ መልካም ወገኖች በሚደረግላቸው ድጋፍ እስረኞችን መጠየቅ ፣ አረጋዊያንን በመደገፍ በየትኛውም ጊዜ በዓልን ሳይጠብቁ ወጣቶቹ በበጎ ተግባር እየተሰማሩ እንደሚገኙ ነግረውኛል።

Via: Gizatu Amare





1 comment

Zelalem Tesfaye January 7, 2025 - 3:05 pm

በየአገሩ ያላቹ ኦርቶዶክሳውያን በርቱ መረጃንም ስለመረጃው እናመሰግናለን
መልካም በአል

Reply

Leave a Comment