banner

የቤንዚን ዋጋ ከ10 ብር በላይ ጨምሯል። በተደጋጋሚ እንደተገለጸውም የዋጋ ንረት አዙሪቱ ቀጥሏል፣ ገና ይቀጥላል።

ታህሳስ 22 ቀን 2017 የገንዘብ ፓሊሲ ኮሚቴ ገጽ 2 ላይ ባቀረበው ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ግምገማ መሰረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ 15% ቀንሷል። ቡናና ወርቅ ዋጋ በመጨመሩ የውጭ ክፍያ ሚዛንም ተሻሽሏል።

የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ያለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩና የመንግስት የውጭ ክፍያ ሚዛን በመዳከሙ ምክንያት እንዳልሆነም ሪፖርቱ ግልጽ አድርጓል።

ይህ ማለት የነዳጅ ዋጋ የመጨመሩ ምክንያቱ የብር የመግዛት አቅም በውሳኔ እንዲዳከም መደረጉ እንጂ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መጨመር እንዳልሆነ ያመላከተ ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አዙሪት መቆምያ ጠገግ እንደሌለውም ሂደቱ በቂ ገላጭ ነው።

የብር የመግዛት አቅም ሲዳከም ኢኮኖሚው ውስጥ ያልነበረ ተጨማሪ ብር እንዲፈጠር ግድ ይላል። ምርትና ምርታማነትን ተከትሎ ያልተፈጠረ ብዙ ብር ከጥቂት ምርት ጋር ሲጋፈጥ ዋጋ ንረት መከተሉ የማይቀር ነው።

የዋጋ መናር የገንዘብ የመግዛት አቅምን ያዳክማል። የብር የመግዛት አቅም መዳከም የውጭ ምንዛሪ አቅምን ያንራል። የውጭ ምንዛሪ አቅም መናር ደግሞ የዋጋ ውድነትን ያስከትላል። የውጭ ምንዛሪ አቻ ትመና መናርን ተከትሎ የብር የመግዛት አቅም ይዳከማል።

የብር መግዛት አቅም መዳከም የዋጋ ንረት፣ የዋጋ ንረት ተጨማሪ የብር ፍላጎት፣ ተጨማሪ የብር ፍላጎት ተጨማሪ ብር መፈጠርን፣ የብር መብዛት የገንዘብ ግሽበትና የዋጋ ንረትን ያስከትላል። አዙሪቱ ይቀጥላል።

የኢኮኖሚ ባለሙያ ሙሼ ሰሙ

3 comments

Bewketu Zerihun Tesfa January 7, 2025 - 7:32 pm

ተሯሩጠህ ኑሮህን እንዳትደጉም፤ ራስህን ቤተሰብህን እንዳትረዳ በብዙ ችግሮች ይተበትቡህና አቅም ያሳጡሃል፤ ከዚያ በአላት እየጠበቁ የማእድ ማጋራት ብለው ያላግጡብሃል። ቤተመንግስት ጠርቶ አበላሁህ ይልና ገና ቤትህ ሳትደርስ በእንደዚህ አይነት ዜና ጭው ያደርግሃል።
መንግስት ግን ምን አስቦ ነው?
የፈረደበት ደሞዝተኛ ሣሙና፣ዘይትና ስኳር ላይም ማስተካከያ ተደርጓል የምል ትርጉምም አለው። ለሠራተኛ ምድር ስኦል ሆናለች።

ቤንዚል ፣ናፍጣን፣ኪሮሲን በየሶስት ወሩ እየጨመረ
ዶላሩንም ከ75 ብር ጀምሮ 6 ወር ሳይሞላው 125 ደርሷል።
የሰራተኞች ደሞዝ ግን ከ አምስት አመት አንዴ አይጨምርም
ስለዚህ በዚህ ሁኔታ እንዴት ባላንስ ይመጣል???

Reply
Kirubel Feleke January 7, 2025 - 7:33 pm

ህዝቡ እያየ ያለው ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ብቻ ነው። ነገ ለጉሮሮው ምን እንደሚበላ የማያስብ ትውልድ እየተፈጠረ ነው ያለው ያሳዝናል💔

Reply
Sewasew More January 7, 2025 - 7:33 pm

ጁንታ እያላችሁ ገና ጁንታ ይገባላችዋል

Reply

Leave a Comment