0
#FastMereja I የተዋህዶ ኤክስፖ አካል የሆነው የጥምቀት ኤክስፖ የንግድ ትርኢት እና ባዛር ለመጀመሪያ ጊዜ በከተማችን አዲስ አበባ በኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።
ማርኮናል ኤቨንት ኦርጋናይዘር ከኢኦተቤ ጠቅላይ ቤተክህነት ፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከኬብሮን የዝግጅት አጋፋሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር የሚዘጋጁት ይህ ኤክስፖ ከዛሬ ጥር 03 እስከ 09/2017 ዓ.ም ለተከታታይ 7 ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል፡፡
በዚህ ልዩ ኤክስፖ የምሽቱ መርሃ ግብር ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ማህበራት፣ ህብረ ዘማሪያን እንዲሁም በርካታ ዘማሪያን እና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ታላላቅ የዝማሬ እና መንፈሳዊ የኪነ-ጥበብ ጉባኤዎች የሚኖሩ ሲሆን ከ42 በላይ የሆኑ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሰ/ት/ቤቶች መንፈሳዊ ሽልማት የሚያስገኙ የጥያቄ እና መልስ እንዲሁም የሥነ-ግጥም ውድድር የሚያካሂዱ ይሆናል፡፡





1 comment
መኪናዋን ብትሸልሙኝና ሂወቴ ቢቀየር