banner

ጥምቀትን በአምሳለ-ዮርዳኖስ: ምንጃር ሸንኮራ

ጥምቅት አንዲት ናት፣ ክርስቶስ ነው ጥንት የመሠረታት።

ምንጃር ሸንኮራ ከሁሉ በፊት በታላቁ ንጉሥ ዐፄ ዳዊት ቀዳማዊ (የዐፄ ዘርዓያዕቆብ አባት) እና በዐፄ ልብነድንግል የተመረጠች ቡሩክ ምድር ናት።

ታሪኳን ወደኋላ ሲመለከቱ ከ1380 ዓ.ም ጀምሮ ኃያላኑ የከተሙባት፣ ፈቀዷትና የወደዷት ናት። አሻራው ዛሬም በእነ ሸንኮራ ባልጪ አማኑኤል ጥንታውያን ንድፍና ጠልሰም ሕያው ነው።

ይኸ ገናና ስሟና ክብሯ ዛሬ ድረስ ኅልው ሆኖ፣ ገዝፎና ተውቦ በሸንኮራ አምሳለ-ዮርዳኖስ በከተራው የ44 ታቦታት መዳረሻ፣ በጥምቀቱም የክርስቶስን ጥምቀት ማክበሪያ ነው።

በየዓመቱ ከጥር 9 ጀምሮ ከ2-3 ሚሊዮን ምእመን በረከት ሊካፈል ከመላው ኢትዮጵያ እና ሌሎች ዓለማት ሸንኮራ ይገባል።

ምንጃር-ሸንኮራዎችም የዶፋ ሚካኤል፣ የሳማ ሰንበት፣ የታላቁ ሸንኮራ ዮሐንስ፣ የአረርቲ ማርያም ልጆች፣ ዘካሪዎች ናቸውና እንግዳ አቀባበልን ከአብርሃም፣ መስተንግዶን ከጠቢቡ ሰለሞን የወረሱ ናቸውና በክብር በማዕረግ በጥልቅ ኃይማኖትዊ ዕሴት ይቀበሉዎታል።

ጥቀትን በሸንኮራ አምሳለ-ዮርዳኖስ እናክብር።





1 comment

Firom Sa January 13, 2025 - 12:42 pm

ተረት ተረት 🤔

Reply

Leave a Comment