banner

ዛቻ እየደረሰባት የሚገኘው የካይ ሃቨርትዝ ባለቤት !

የአርሰናሉ አጥቂ ካይ ሃቨርትዝ ሚስት ትናንት በማንቸስተር ዩናይትድ በኤፍኤ ዋንጫ በተሸነፉበት ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ እየደረሰባት የሚገኘውን ማስፈራሪያ ተናግራለች፡፡

የ25 አመቱ አጥቂ በትናንትናው ወሳኝ ጨዋታ ላይ ያሳየው ደካማ አቋም እንዲሁም የሳታቸው የግብ እድሎች ከዛም በተረፈ የሳተው ወሳኝ ፍጹም ቅጣት ምት በብዙዎች ሲያስተቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ከእሱም አልፎ በባለቤቱ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለያዩ ዛቻዎች እየደረሷት እንደሆነ አስታውቃለች፡፡
የጀርመናዊቷ የካይ ሃቨርትዝ ባለቤት ሶፊያ የደረሱባትን የማስፈራሪያ መልዕክቶች በኢንስታግራም ገጿ ላይ አስፍራለች፡፡

የስሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የደረሰባትን ዛቻ እና ማስፈራሪያ ለፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን ወንጀለኞቹን ለመለየት ከልዩ ባለሙያዎች ጋር በጋር እየሰራ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የተጨዋቹ ሚስት በምላሿ እባካችሁ በምታደርጉት ነገር ማፈር አለባችሁ፤ከዚህ የተሻለ ነገሮችን ማድረጋችን አይቀርም ስትል ተናግራለች፡፡

ጥንዶቹ እ.ኤ.አ ከ2018 ጀምሮ በፍቅር አብረው የኖሩ ሲሆን ባለፈው አመት ተጋብተው አሁን ላይ ባለቤቱ ነብሰ ጡር እንደሆነች ታውቋል፡፡

በይገደብ አባይ

8 comments

Absí Jøh's January 13, 2025 - 2:17 pm

ሃዬ 🤣

Reply
Bereket Wondimu January 13, 2025 - 2:18 pm

እና ያረገዘው ካይ ነው እንዴ😊?

Reply
Polijohnny Yohannes Solomon January 13, 2025 - 2:18 pm

እግርኳስ መዝናኛ መሆኑንም እረስተውታል

Reply
Samuel Gunner January 13, 2025 - 2:18 pm

እኔ አለሁ፣ አትፍሪ በሏት! 🚶🔥

Reply
Eliâs Abãynéh January 13, 2025 - 2:19 pm

የተመገበውን በሙሉ ለሷ እያስረከበ 🤭😂😂😂

Reply
Bitaniya BT January 13, 2025 - 2:19 pm

የአርሰናል ደጋፊ በየ አገሩ ወያላ ነው ማለት ነው!
ዘራቸው አንድ ነው! ስንጥር ሁላ😝

Reply
Lij Abrish January 13, 2025 - 2:20 pm

አጥቂ ነዉ ያልከኝ

Reply
Emu Teklu January 13, 2025 - 2:20 pm

ኢትዮጵያዊያን ደጋፊዎች እንደሚኖሩ የታወቀ ነው😁🤣🤣

Reply

Leave a Comment