የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ የጥምቀትና ከተራ በዓል በከተማዋ መከበሩን አስመልክቶ ምስጋናቸውን አቀረቡ
የሰላም እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነችው የሀዋሳ ከተማ ታላላቅ እና ግዙፍ ሀይማኖታዊና ሌሎች ሁነቶችን ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ማስተናገጓ የከተማዋን ተመራጭነት የሚያጎላው ስለመሆኑ ተናግረዋል።
የዚህ ማሳያ ከሆኑ በዓላት አንዱ የሆነው የከተራና የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ መላውን የበዓሉን ታዳሚያን እና እንግዶችን ባሳተፈ መልኩ መከበሩ ጠቋሚ ስለመሆኑም ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ የከተማው ነዋሪ፣ የፀጥታ ሀይሉ እና የሀይማኖት ተቋማት ከምንጊዜውም በላይ ይህን ሀይማኖታዊ በዓል በከተማዋ ያሀ ምንም የፀጥታ ስጋት ለማክበር ያደረጉትን ጥረት አመስግነዋል ከከንቲባው።
በተለያዩ ጊዜያት በከተማዋ መሰል ሁነቶች መከበራቸው የሀዋሳን ተመራጭነት የሚያጎላው ነው ያሉት አቶ መኩሪያዬ ይህም የቱሪዝም ኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ከፍ ስለማድረጉ በማስረዳት ነው የጠቆሙት።
ነገና ተነገ በስቲያ በከተማዋ የወጡ አድባራት በተመሳሳይ መልኩ መዕመኑ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በማክበር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ቅንጅታዊ አሰራር እንደሚደረግም አያይዘው ተናግረዋል።
0





2 comments
💕💕💕💕
ይመሰገናሉ እድሜ ይስጣቸው ።