banner

የዉጪ ምንዛሪ ለዉጡን ተከትሎ ከግምት ዉስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ

የዉጪ ምንዛሪ ለዉጡን ተከትሎ ከግምት ዉስጥ ያስገባ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግ ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጥሪ ቀረበ

መንግስት ለረጅም ጊዜ ሲጠብቅ የነበረውን የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪ ተግባራዊ ቢያደርግም አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ግን ተጨማሪ ክለሳዎች እንዲደረጉ እየጠየቁ መሆኑን ካፒታል ጋዜጣ ዘግበዋል።

የሚኒስትሮች ም/ቤት ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 36ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ጭማሪን ያፀደቀ ሲሆን ይህም ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል።

አገልግሎቱ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያዉ እስከ 200 ሜጋዋትስ ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞችን ድጎማ እንደሚያደርግ ገልጿል ። ማሻሻያው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን ደንበኞች ታሳቢ አድርጓል ቢባልም የተደረገው ጭማሪ በዓመት ዉስጥ 122 በመቶ ደርሷል።

ይሁን እንጂ ከማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ ጋር በተገናኘ እንደ አለም ባንክና የአለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምን (አይ.ኤም.ኤፍ) የመሳሰሉ አለምአቀፍ አጋሮች የተለያዩ ድጋፍ ከማድረጋቸው ጋር ተያይዞ መንግስት ያፀደቀውን የታሪፍ ጭማሬ በድጋሚ እንዲያጤነው መጠየቃቸው ነዉ ለማወቅ ተችሏል ሲል ካፒታል ዘግበዋል።

10 comments

Michael Miki January 20, 2025 - 7:36 am

ከመንግስት ጋር ተባብረው ሊጨርሱን ነው አሳባቸው! አይ ምዕራባዊያ ከዛ ደሞ ህዝብ ተራበ ስንዴ እንርዳ ይላሉ እራሳቸው እያደሄዩ! ለህዝብ የሚያስብ መሪ እስካልመጣ ገና ይቀዝኑብናል! 😭

Reply
Mõĥãmmêď Ĩbňū Ŝēmmëř January 20, 2025 - 7:38 am

ድል ለኩራዝ💪💪

Reply
ገን ስልጤ January 20, 2025 - 7:39 am

አንሞትም አልናቸው። መንግስት በቃ ተላላኪ አስፈፃሚ ሆኖ ቀረ ማለት ነው።

Reply
Kenaan Dawit January 20, 2025 - 7:43 am

አንድ አፍታ ይግዛን::

Reply
Demeke Gichamo January 20, 2025 - 7:44 am

Imf is new owner of Ethiopia

Reply
Atnafu Alemayehu January 20, 2025 - 7:46 am

አባይ 80 ቢሊዮን ጠየቀ አሉ😁😁😁😁

Reply
Kifle Tesfaye January 20, 2025 - 7:47 am

ዓለም አቅም የገንዘብ ተቋማት ቀንደኛ የሕዝብ ጠላት ሆነዋል። ሕይወታችን በእነርሱ የተያዘች ይመስል እያስፈራሩ፣እይስጨነቁ ጉዟቸውን ቀጥለዋል። እንያችሁ ያሉ ይመስላሉ???

Reply
Abraham Kassa January 20, 2025 - 7:48 am

ገና ምን ጉድ እንሰማለን

Reply
Tadi Ma Atse Teshe January 20, 2025 - 7:50 am

እንኳን ወደ ዘመናዊው ቅኝ ግዛት በሰላም ገባን የማንወጣው ቅርቃር 🤦🏼‍♂️🤔

Reply
Keka Gezahegn January 20, 2025 - 7:52 am

እና ተሽጠናል አይደል 😁😁😁 ምን ጠብቀን ነበር

Reply

Leave a Comment