banner

የአዲስ አበባ የግማሽ ዓመት የፍቺ መጠን፤ ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ በ34 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው መንፈቅ ዓመት በይፋ የተመዘገበው የፍቺ መጠን፤ አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ34 በመቶ መጨመሩን የከተማይቱ የሲቪል እና የነዋሪነት ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ። በዚሁ ጊዜ የተመዘገበው የጋብቻ መጠን፤ ባለፈው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከተመዘገበው በሰባት በመቶ መቀነሱንም ኤጀንሲው ገልጿል።

ተቋሙ ይህን የገለጸው የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ፤ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 13 በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው። የመታወቂያ ስርጭት፣ የልደት እና የሞት ምዝገባ፣ ያላገባ የምስክር ወረቀት፣ የማስረጃ የማረጋገጥ ስራን ለመዲናይቱ ነዋሪዎች የሚሰጠው ኤጀንሲው፤ በከተማይቱ የተከናወኑ ጋብቻ እና ፍቺዎችንም ያከናውናል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፤ መስሪያ ቤታቸው ባለፉት ስድስት ወራት የመዘገበው ፍቺ 3,769 መሆኑን በዛሬው መግለጫ ላይ አመልክተዋል። ኤጀንሲው ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የመዘገበው ፍቺ 2,832 እንደነበር የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የዘንድሮው የፍቺ መጠን በ34 በመቶ ጭማሪ ያሳየ እንደሆነ አስገንዘበዋል።

በአንጻሩ ባለፈው መንፈቅ ዓመት በኤጀንሲው የተመዘገበው የጋብቻ መጠን፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲወዳደር በሰባት በመቶ መቀነሱን ተቋሙ አስታውቋል። የሲቪል እና የነዋሪነት ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ ባለፈው ስድስት ወራት የተመዘገበው የጋብቻ መጠን 15,574 ነው። መስሪያ ቤቱ በዚሁ ጊዜ ለመመዘገብ አቅዶ የነበረው የጋብቻ ብዛት 21,674 ነበር።

የከተማይቱ ነዋሪዎች “አስገዳጅ ሁኔታዎች ካላጋጠሟቸው በስተቀር” ወደ ተቋሙ በመምጣት ወሳኝ ኩነቶችን የማስመዝገብ ልምዳቸውን “አነስተኛ” መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የዘንድሮው የጋብቻ መጠን ለመቀነሱ ይህ አንዱ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል። “ሰዉ፤ ፎቶ መነሳት ብቻ ጋብቻ ይመስለዋል” ያሉት አቶ ዮናስ፤ በህብረተሰቡ ዘንድ ጋብቻን ማስመዘገብ ያለውን ጥቅም እና አስፈላጊነት “በአግባቡ ያለመረዳት” ችግር እንዳለ ጠቁመዋል።

Via: ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

10 comments

Ke'ti Yiga Begi January 21, 2025 - 4:32 pm

Yemigermew dehaw ezih bota lay yelum egziahbiher yimesgen amen

Reply
Tegegn Chinkisso January 21, 2025 - 4:34 pm

መፋታትን እጠላለሁ ይላል ታላቁ መጽሀፍ ቅዱስ።የፊች መብዛት ሀገራችን ትልቅ አደጋ ዉስጥ መሆኑሀን ያሳያል።

Reply
Ruhama G. Girmatsion January 21, 2025 - 4:34 pm

yegna saykoter Luwam Habenom 😭😭😂

Reply
Lemi Yohannes January 21, 2025 - 4:34 pm

በዚህ ኑሮ የእራስ አመል መቻል እራሱ ከባድ ነው እስኪ ኑሮ ይቀንስ ፍችውም ይቀንሳል ሰው እኮ በኑሮ አቅሉን አጣ

Reply
Kinfe Gabriel January 21, 2025 - 4:35 pm

አቤቱ ያላገባን በነፃነት የፈለግነውን date አርገን በድተን የምናድር ምነኛ የታደልን ነን

Reply
አባ ሳሙኤል January 21, 2025 - 4:39 pm

ቺት ማድረግ ከተማዋ ላይ ኖርማል ሆኖ እንዴት አይፋቱ 😔 አሁን ላይ የገዛ ሚስቴን ወገቤ ላይ በገመድ አስሬ ሄዳለዉ እንጂ ከባድ ነዉ ጊዜዉ🥶

Reply
Abu Anes AN Negesse January 21, 2025 - 4:39 pm

እኛ አልሰማንም በግሉ የተጋባ ሊሆን ይችላል😠 በወግ በማዕረግ የተጋቡት አሉ ያዝልቅላቸው እስከመጨረሻ🙏

Reply
የፍቅር ቀጠሮ January 21, 2025 - 4:41 pm

የብልጽግና እቅድ ለማፋታት ነበራ 🤣🤣

Reply
የልብ ቁስል ቪቫዊቷ January 21, 2025 - 4:43 pm

ሳይግባቡ እየተጋቡ እኮ ነው ሲጋቡ ሚፉቱት😭😭😭 ሰው ምን ይለኛል ተብሎ ለታይታ ና ለፎቶ ተብሎ ሚመሰረት ትዳር ነው አብዛኛው 🤗

Reply
Amen Amen Amen January 21, 2025 - 4:44 pm

ሰዎች ሳትግባቡ አትጋቡ

Reply

Leave a Comment