በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ 80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እንድቀጣ ፍርድቤቱ ወስኗል ።
ወንጀሉ የተፈፀመው ህዳር 5/2017 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ሚችሌ ሆለና አከባቢ ስሆን ተከሳሽ ወጣት ቶሎሳ ዘውዴ የተባለው ግለሰብ ከምሽቱ 6 ሰዓት ላይ የ 80 ዓመት አዛውንት ብቻቸውን ሚኖሩበትን መኖሪያ ቤት ሰብሮ በመግባት ድርግቱን መፈፀሙን በክሱ መዝገብ ላይ ተጠቅሷል ።
የወረዳ ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አዉሎ ወንጀሉ መፈፀሙን የሚያስረዱ የሰውና የሠነድ ማስረጃዎችን አደራጅቶ ለዐቃቤ ህግ አቅርቧል ።
ዐቃቤ ህግ ፣ ተከሳሹ አዛውንቷ በቤቷ ለብቻ እንደምትኖር አውቀው ቤት ሰብሮ በመግባት መከላከል በማትችልበት ሁኔታ ድርጊቱን እንደፈፀመ የሚያስረዱ ማስረጃዎች አስደግፎ ለዲላ ዙሪያ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሱን አቅርቧል።
ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ የተመለከተው የዲላ ዙሪያ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ተከሳሽ ወጣት ቶሎሳ ዘውዴ የተባለው ግለሰብ የፈፀመውን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ድርጊት በምስክር እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጥ ጥር 14 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ በ 10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድቤቱ ወስኗል።
10 comments
እግዞኦ ምን አይነት እንስሳ የሆነ ሰው ነው
ይሄ ሬሳ ነዉ ቅበሩት😏
እስከ 80 ዓመት እሙሙሙ ይኖራል እንዴ😂👀
አረ እንዴት ቻለበት🙄🙄 ደነዝ😏
ይሄን በቁሙ ነው መቅበር ማይሰማ ጉድ የለም ዘንድሮ
እና ቴሌ ብር ነው ስፖንሰሩ
በዚህ ጉዳይ ኢትዮ ቴሌኮምም እጁ ሳይኖርበት አይቀርም🙄
የጤንነቱ ጉዳይ አሳሳቢ ነው?
እስከ 80 ዓመት እሙሙሙ ይኖራል እንዴ😂👀
አዬ ሰው አዬ ሰው ትላለች ቀበሮ ለሰው ሞት አነሰው 👍