banner

ጋዜጠኛ ናፍቆት ትዕግስቱ የአፍሮ ሺክ ብራንድ አምባሳደር ሆነች!

#FastMereja I የግል እንክብካቤ ምርቶችን በማከፋፈል የሚታወቀው አንጋፋው የትም ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ላለፉት 20 ዓመታት ምርቶችን ለተጠቃሚዎች ሲያቀርብ ቆይቷል። የትም ትሬዲንግ «አፍሮ ሺክ» የተባለውን አዲሱን ምርቱን በጥራት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በአዲስ መልኩ ለተጠቃሚዎቹ ይዞ መምጣቱን ዛሬ ጥር 20/2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል አስታወቀ።

«አፍሮ ሺክ» የጸጉር፣ ቆዳ እና ሰውነት እንብካቤ ምርቶች ሀገር ውስጥ የሚገኙ ግብዓቶችን በመጠቀም በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደቀረቡ ነው የተገለፀው። ምርቶቹ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ቅባት እና ሎሽኖችን ሲያካትቱ በራሱ ፋብሪካ ተመርተው በተጣጣኝ ዋጋ ለማህበረሰቡ መቅረቡ ነው የተገለፀው።

የትም ትሬዲንግ ጋዜጠኛ ናፍቆት ትዕግስቱን ለአንድ አመት የአፍሮ ሺክ ብራንድ አምባሳደር በመሆን ምርቱን እንድታስተዋውቅ በዛሬው እለት በሚሊዮን ብሮች ስምምነት ፈፅማለች።





4 comments

Mayka Deju January 28, 2025 - 8:55 am

ይገባታል

Reply
Simegnew Setegn January 28, 2025 - 8:55 am

ወደ EBS ትመለስ!የEBS ድምቀት ነች!

Reply
Umu Maria January 28, 2025 - 9:03 am

She is beautiful

Reply
Yosef Belay Bizuneh January 28, 2025 - 9:03 am

እንኳን ከዘመነ የክብር ዶክትሬት ወደ ዘመነ ብራንድ “አምባሳደር” አሸጋገረን

Reply

Leave a Comment