banner

5ኛው ፊንቴክስ የፈርኒቸር የቤተ ውበትና የግንባታ አጨራረስ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ።

#FastMereja I «ንግድዎን በመቅረዝ ላይ ያኑሩ» በሚል መሪ ቃል ፊንቴክስ FINTEX የፈርኒቸር፣ የቤተ-ውበት እና የግንባታ አጨራረስ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ቴክኖሎጂዎች ዓለም አቀፍ አውደ-ርዕይ ከጥር 22 – ጥር 25 ቀን 2017 ዓ/ም በሚሊኒየም አዳራሽ ለ5ኛ ጊዜ መካሄድ ጀመሯል፡፡

ፊንቴክስ አውድ-ርዕይ ላይ የአገር ውስጥ አምራቾችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰባሰብ ከመላ አገራችን ከሚመጡ ከመንግስት፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከዲፕሎማቲከ ማህበረሰብ እና ከበጎ አድራጎት ተቋማት፣ በመገንባት ላይ ከሚገኙ ባንኮች፣ ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ማዕከላት፣ ሲኒማ ቤቶች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ ከአነስተኛና ጥቃቅን በማደግ ላይ ለሚገኙ የፈርኒቸር አምራቾች እንዲሁም ወኪል ሆነው በከልል ከተሞች ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በፈርኒቸር፣ በቤተ-ውበት እና በግንባታ አጨራረስ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የሚተጉ ግዙፍ የአገር ውስጥ አምራቾች ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል መድረከ እንደሆነ ተነግሯል።

ከ4000 የሚበልጡ የዘርፉ ባለሙያዎች እና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት ከስመጥር የሃገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር የንግድ ትስስር እንደሚያድርጉ ይጠበቃል።

ኤክስፖው ፕራና ኤቨንትስ እና አፍሪካን ትረስትድ ፓርትነርስ በጋራ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡





Leave a Comment