banner

በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከ

በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳዬ እንደገለፁት በመዲናዋ 429 ሺህ 829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል፡፡

ይሁንና እስካሁን ባለው ሂደት 228 ሺህ 222 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር መፈፀማቸውን በመግለፅ ይህም የዕቅዱ 51 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አክለውም የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

የቤትና ቦታ ግብር በተለምዶ የአፈር፣ የቤትና ጣሪያ በሚሉና መሰል ስያሜዎች እስከ የካቲት 30 ድረስ የሚሰበሰብ የግብር አይነት መሆኑ ተገልጿል።

10 comments

Abera Lemma Begna February 4, 2025 - 7:21 am

La batasab kifalu endayielu becha

Reply
Mote Jesus February 4, 2025 - 7:21 am

ወቸ ጉድ

Reply
Cheguvera Cheguvera February 4, 2025 - 7:21 am

ፀሀይ የምንሞቅበትስ ግብር መች ነው የምንከፍለው ?

Reply
Rutha Tenkir February 4, 2025 - 7:22 am

ትንሽ ሲቆይ ለምናገኛት አየር እንዳያስከፍሉን እሰጋለሁ 😔

Reply
Fraser Pryce February 4, 2025 - 7:23 am

Egziabeher beseten meder laye lemenenorbet kefelu yemil dedebe mengest

Reply
Efeson Grace Jr. February 4, 2025 - 7:23 am

ምነው የአዲስ አበባ ሕዝብ ካልጋጥን አላቹሳ
ትርፉ ለተከራይ ማህበረሰብ መሆኑን ዘነጋቹሳ ጅቦች

Reply
HA MU February 4, 2025 - 7:23 am

እናት ፓርቲ ያቀረበችው ክስስ ?

Reply
Azma Menzo February 4, 2025 - 7:23 am

የሆነ ፓርቲ “ተከራክሬ ተካስሼ ሐሳቤ ተቀባይነት አግኝቶ ውድቅ አስደረግት”አላለም ነበር ወይ ወይ ወይ ወይ?🤔

Reply
Dagim Worku February 4, 2025 - 7:24 am

እናት ፓርቲ አስቀረሁት አላለም 🤔🤔🤔

Reply
Natman Ab February 4, 2025 - 7:24 am

ነገሮች እንዲህ ከቀጠሉ እዚህ ሀገር ለመኖርም ግብር መክፈላችን አይቀርም😪👀

Reply

Leave a Comment