banner

የሉሲ ቅሪተ-አጽም በአውሮጳ ቤተ-መዘክር ለዕይታ ሊቀርብ ነው

በሰው ልጆች አፈጣጠር ሣይንሳዊ ምልከታ 3.18 ሚሊዮን ዓመት እድሜ እንዳለው የሚገመተው የሉሲ ወይንም ድንቅነሽ ቅሪተ-አጽም አውሮጳ ውስጥ ለዕይታ ሊቀርብ ነው ። በሰሜን ምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል አፋር ውስጥ ከግማሽ ምእተ ዓመት በፊት የተገኘው ይህ ቅሪተ-አካል ከዚህ ቀደም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለዕይታ ተወስዶ ነበር ። አሁን በአውሮጳ፤ ቼክ ዋና ከተማ ፕራኅ ብሔራዊ ቤተ-መዘክር ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ ይቀርባል ተብሏል ።

10 comments

Eskendr Ayalew February 4, 2025 - 4:27 pm

በእግዚአብሄር እኔ ላድርሳት!🙏😭

Reply
መቅዲ አባቴ ወድሃለሁ February 4, 2025 - 4:29 pm

መልካም መንገድ በሰላም ሄዳ ትምጣ ኡፍፍ በናፍቆት ማለቃችን ነው😥😥

Reply
Ya Bu February 4, 2025 - 4:30 pm

እቃዎቿን የሚይዝ ከፈለገች አለው

Reply
Natinael Samuel February 4, 2025 - 4:31 pm

ሉሲ እኮ እኔ ነኝ ካላመናችሁ ኑና ቤተሰብን ጠይቁ🙏🙏🙏🙏

Reply
Teddy Fassil February 4, 2025 - 4:31 pm

እኛም ከሞትን ከዘመናት በሓላ እንዳይሆን ብቻ አውሮፓ ምንሄደው!!!

Reply
Metshet Mesfin February 4, 2025 - 4:32 pm

ሞግዚት አትፈልግም🤣

Reply
Mi Nte February 4, 2025 - 4:32 pm

እኔ ደምና ስጋ ያለኝ የ 30 ዓመት ሰውዬ ከእናቴ ቤት አልወጣውም አፅም አንዴ አውሮፓ አንዴ አሜሪካ 😭ወይኔ በላቸው

Reply
Hannah February 4, 2025 - 4:38 pm

ከኛ በቁም ካለነዉ በላይ ዓለሙን ታካልለዉ ወይኔ ወይኔ😭

Reply
ጥቁር አዝሙድ February 4, 2025 - 4:38 pm

ለሽርሽር. ነው ኩላሊቷን. አደራ

Reply
ማህደር የሽወንድ February 4, 2025 - 4:38 pm

ብዬ ብዬ በአፅም ልቅና🙄

Reply

Leave a Comment