የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ዓመታት በክልሉ ሰላምና ደህንነት ዘርፍ እጅግ አስደናቂ ስኬት እንዳስመዘገበ አስታውቀዋል።
የኮሚሽኑ ትልቅ ፕሮጀክት በመሆን እየተሰራ የነበረው በሕብረተሰብ ተሳትፎ እየተገነባ የነበረው የፖሊስ ፅ/ቤት እና የመረጃ መቀበያ ፕሮጀክት ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ ከ640 በላይ የመረጃ መቀበያ ተቋማትና ከ36 በላይ የፖሊስ ጣቢያዎችን በመገንባት አገልግሎቱን በእጅጉ ማሻሻል መቻሉም ታውቋል።
የፓሊስ ተቋማት በጀት በክራይ ቤት ከማለቁ በላይ የፖሊስ አባላቱ ባልተመቻቸ ሁኔታ ለህዝቡ አግልግሎት እየሰጡ የቆየ ሲሆን ይህንን 100% በሚባል ሁኔታ በክልሉ ውስጥ በመቅረፍ ለክራይ የሚለውን የበጀት ብክነት በመቆጣጠር በጀቱን ራሱን በግብዓት እና በሌሎች ነገሮች እንዲያጠናክር ያስቻለ እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ እና የተሳካ ፕሮጀክት በመባል ተገልፆል።
በፖሊስ ኮሚሽኑ ከተሰሩ ሪፎርሞች መካከል በተጨማሪነት የፖሊስ ኮምሽኑ ተሽከርካሪዎች በተቋሙ በተገነባው የፖሊስ ኮምሽኑ ገራዥ ጥገናዎችን እንዲያካሂድ የሚያስች ገራዥ ተገንብቷል፣ የፖሊስ አባላቱ እና ቤተሰቦቻቸው ባልተጉላላ ሁኔታ የህክምና አገልግሎት በተመጣጣኝ ሁኔታ እንዲያገኙ የሚያስችል የህክምና አገልግሎት መስጫ ጤና ጣቢያ በመገንባት የፖሊስ ኮምሽኑ የውስጥ አቅሙን ማጠናከሩም ተገልፆል።
የሲዳማ ክልልን ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ በማድረግ 24 ሰዓት ያለተቋረጠ የጸጥታ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። ኮሚሽኑ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ዘመናዊ የፀጥታ ክንውኖች እንዲፈጠሩ በካሜራ የታገዘ የፀጥታ አደረጃጀት ለመፍጠር በእቅድ ደረጃ እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም በሀዋሳ ከተማ ላይ ተግባራዊ በተደረገው የዘመናዊ የፀጥታ አደረጃጀት የመፍጠር ሂደት ላይ በተሰራው የላቀ ስራ መሰረት የደህንነት ካሜራዎችን በመግጠም እና የንግድ ተቋማትም ይህንን የደህንነት ካሜራ እንዲገጥሙ በማስተባበር ከ90% በላይ የሚሆኑው የከተማዋን አካባቢዎች በዘመናዊ የደህንነት ካሜራ ቴክኖሎጂ በማስታጠቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰላምና ደህንነት አገልግሎት እንዲኖር መቻሉንም ታውቋል።
በተጨማሪም በሀዋሳ ከተማ በፋይበር ኔትወርክ የሚሰሩ ካሜራዎችን በመትከል ውጤታማ በሆነ መንገድ የሰላምና ደህንነት ስራዎች ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑም ተገልፆል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ በህገ-ወጥ ተግባር ላይ ብሎም ህዝብን በሚገባው ልክ ባላገለገሉ አባላትን እና አመራሮችን በመለየት እና በመገምገም ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ በተቋሙ ውጤታማ የህዝብ አግልግሎት በመስጠት እና ታማኝ ተቋም በመገንባት በኢትዮጵያም ለሌሎች ክልሎች አርአያ የሆነ ተቋም መሆኑም ታውቋል።
ከክልሉ አልፎ በአጎራባች አካባቢዎችም የሚታዩ ትንንሽ ግጭቶችን በትኩረት በመመልከት የሚታዩትን የደህንነት ችግሮችን ወደ ሰላም በመቀየር ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ሲሉ ከሰሞኑ በወላይታ እና በሲዳማ ክልል ድንበር የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮምሽን በጋራ ከአጎራባች አቻ ተቋማትን እና አሰተዳዳሪዎች ጋር በመመከር የወሰዱት እርምጃ የሚደነቅ መሆኑን የአከባቢው ማህበረሰብ ገልፀዋል።





1 comment
ጭራሸ እኔ አላምንም 😂😂😂