banner

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በይፋ ተጀመረ። ግንባታውን ያስጀመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ናቸው።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በአፍሪካ ሕብረት መሠብሰቢያ አዳራሽ አካባቢ የሚገነባውን የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል የመጀመሪያ ዙር የግንባታ ሂደት አስጀምረዋል።

ፕሬዝደንቱ ፕሮጀክቱን ባስጀመሩበት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከ2015 ዓ.ል ጀምሮ የፕሮጀክቱ ግንባታ በአግባቡ እንዲከወን የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ እንደቆየ አንስተዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰያሚነት የተቋቋመውና ግንባታውን በበላይነት የሚመራው ኮሚቴ ላለፉት ሁለት አመት አጠቃላይ የቅድመ ዝግጅትና የጨረታ ስራዎችን ያለ ምንም ክፍያ ሲሰራ እንደቆየም የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ጠቅሰዋል።

ሸይህ ሀጅ ኢብራሂም አክለውም የአለም አቀፉ ኢስላማዊ ድርጅት (ራቢጣ) ፕሮጀክቱን ለማስገንባት ቃል በገባው መሰረት ገንዘብ ለመልቀቅ የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝበ ሙስሊሙን ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመመለስ በመጅሊሱ የውስጥ አቅም ግንባታው እንዳስጀመረ አመላክተዋል።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ እውን እስኪሆን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራም ፕሬዝደንቱ አረጋግጠዋል።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ አበይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በቡላቸው ግንባታውን ለመጀመር እረጅም ጊዜ የወሰደው ፕሮጅክቱን የሚመጥን ዲዛይን ለማዘጋጀትና ለመምረጥ ጊዜ በማስፈለጉ መሆኑን ጠቅሰው የግንባታው ምዕራፍ ያንን ሊያካክስ በሚችል መልኩ እንደሚፋጠን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ለሀገርና ለህዝብ ትልቅ እሴት የሚጨምር በመሆኑን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅድሚያ እንደሚሰጠው የገለፁት ደግሞ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያ ሀጅ ከማል ሀሩን ናቸው።

ዋና ስራ ሥራ አስኪያጁ መሬቱ ከተገኘበት 2012 ዓ.ል ጀምሮ እስከ 2015 ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሰው የለውጡ መጅሊስ ፕሮጀክቱ ካለው ሀገራዊ ፋይዳ አንጻር ትኩረት በመስጠት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤትና አብይ ኮሜቴ አዋቅሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባላት እና በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደርን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተዋል።




10 comments

Hani Boss February 9, 2025 - 5:06 pm

በመጨረሻም👌👌

Reply
Obo Abu Habesha Sth February 9, 2025 - 5:06 pm

ወደፊት ሁለት ሰዎች ይመጣሉ የጀነትን ሽታዋን አያገኙ ከተባሉት ዉስጥ … ለብሳ ያለበሰች ሴት ናት አሉ ! ረሡል ሰ.ዐ.ወ እና ልጆቻችሁን እህቶቻችሁን አድኑ በቅርባችሁ ባለ ሰዉ ትጠየቃላችሁና ..🕰 አደል ወይ የተባለው ሀዲሱ ላይ 😴 ታዲያ ምነው

የአክሱም ሴት ተማሪዎቻችን ጉዳይስ በአላህ ለምንድነው ግን በዚህ ልክ ዝም ልትሉ የፈለጋችሁትን ?😴አረ አላህን ፍሩ😢

Reply
ሶፎንያስ ሚኒሊክ February 9, 2025 - 5:12 pm

ነጃሺ የሚባል ንጉሥ በኢትዮጵያ ታሪክ የለም።

በፈጠራ ታሪክ ሰው አታጭበርብሩ።

Reply
Abineh M Dave February 9, 2025 - 5:20 pm

የእስላማዊ አሸባሪዎች መሰብሰቢያ ኢትዮጵያ ዉስጥጨምን ይሰራል?

Reply
Bîlâl-âl Hâbêsh February 9, 2025 - 5:37 pm

Mash Allah finally

Reply
Solomon Kiros February 9, 2025 - 5:37 pm

ታሪክ ለባለ ታሪክ ተዉለት ህንጻ ስለገነባህ ታሪኩ ያንተ አይሆንምና

Reply
A Fata Hassan February 9, 2025 - 5:47 pm

ማአሻላህ ሲምር ለማየት ያብቃን አላህ ሆይ ለእኔም አቅም ስጣን ልአግዝባት,

Reply
የአጼው ልጅ February 9, 2025 - 5:57 pm

ነጃሽ የሚባል ንጉሥ ነግሶ አያቅም በኢትዮጵያ ውስጥ።

Reply
Tofik Abdella February 9, 2025 - 6:03 pm

Alamdulilha

Reply
Mule Berry February 9, 2025 - 6:16 pm

መገንባት ያለበት ትግራይ ክልል ውቅሮ ነው!

Reply

Leave a Comment