banner

በ2.6 ቢሊዮን ብር ሚድሮክ በሐዋሳ ቅንጡ ሪዞርት ሊገነባ ነው።

#FastMereja I ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሐዋሳ ለሪዞርት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል።

‘ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን ሐዋሳ’ የሚል ስያሜ ያለው ሪዞርቱ በ21 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን፤ እስከ 2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ታውቋል።

የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን የሚያቀርበውን ሪዞርት አጠቃላይ የግንባታ ስራ በ2 ዓመት ጊዜ ውሰጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ቅንጡ የሆነው ሪዞርቱ ትልልቅ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን በብቃት የማስተናድ አቅም ኖሮት የሚገነባ ሲሆን፤ ለሆቴል እና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ተገልጿል።

ሪዞርቱ በግንባታ ሂደት ለ500 ሰዎች እንዲሁም ተጠናቆ ወደስራ ሲገባ ከ350 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

ለሪዞርቱ ግንባታ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።





1 comment

Guch Ye Ab Lij February 13, 2025 - 10:58 am

Be Gujii worqi inante lela ketema alimu fexar Andi KENI yimetal

Reply

Leave a Comment