0
#FastMereja I በምዕራብ ወለጋ ነጆ እናት እና አባቱ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ የጠፋው ልጅ ከሶሰት ቀናት ፍለጋ በኋላ በቁጥጥር ስር ዋለ።
ፈይሳ ፉፋ ነጋሽ የተባለ ተከሳሽ ምሽት አምስት ሰዓት እናት እና አባቱን በጩቤ አንገታቸው ስር በተደጋጋሚ ከወጋቸው በኋላ ከአካባቢው ተሰውሮ የነበረ ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያ ፎቶ ተለቆ ሲፈለግ የነበረ ሲሆን በቄለም ወለጋ ጋዎ ቄቤቲ ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉ ለፋስት መረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
10 comments
አቤቱ ጌታ ሆይ ከዚህ ክፉ ዘመን ጠብቀህ አሻግረን እግዚኦ
ዛሬ ደሞ ስለ ግድያ ብቻ ነው እዚህ ጋ መለቀቁ የግድያ ወንጅልን ማበረታታት መስሎ ነው የሚታየኝ
ኧረ ዘንድሮ ምንድነው የሚሰማው ዜና ሁሉ ፈጣሪ ሆይ ተመልከተን 😓😭😭😭😭
ጆሮአችን መጥፎ ነገር ብቻ እንድንሰማ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጠርን የጉድ ሀገር
እንደዚህ አይነት ከመስማት በደነው ጊዜ ረዝሙን መንገድ ከተጋዙት ጋር መሄድ ይሻል ነበር አይገኝም እጅ
በየሱስ ስም 🥹
ሁልሽም ጨዋ መሳይ ፍለጠው ቁረጠው በማለት የሚያበረታታው ማን ሆኖ ነው እዚህ እግዚኦ ምናምን የምትሉት
አንዳዴ እንደዚህ አይነት ነገር ፖስት ባለማድረግ ተባበሩን ፕሊስ
ፋስት መረጃ ከምትለው ፔጁን የተዘጋው ዶሴ በሚል ብትቀይረው ምንድነው በስመአብ 🙄
የመጨረሻው ዘመን ነው ።
አይ ወለጋ የህዝብ ደም የጠማት አገር ሆናለች እግዚአብሔር ይቅረባት እንጂ