0
የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ቅርጽ በመጠቀም አሸተን በሚል ስያሜ አቶ እንዳለ ተስፋዬ የተባለ ግለሰብ በአሜሪካ የሽቶ ማምረቻ ድርጅት በመክፈት እያሰራጨ መሆኑን ተገልጿል፡፡
ይህም ተግባር የቤተ ክርስቲያኗን መብትና ቅድስና የተዳፈረ እንዲሁም ያለ ገዳሙ ፍቃድ የግሉ የፈጠራ ውጤት አድርጎ በአሜሪካ የአዕምሮ ንብረት ባለቤት አስመዝግቧል ያለው የገዳሙ አሰተዳደር ጽሕፈት ቤት ድርጅቱ ቤተ ክርስቲያኗን ይቅርታ በመጠየቅ ዲዛይኑን እንዲቀይር በጥብቅ አሳስቧል።
አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ የገዳሙ አስተዳዳሪ በማኅበረ ቅዱሳን ከወልድያ ማእከል ሚዲያ ክፍል ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ግለሰቡ ከድርጊቱ እንዲታቀብ ቢጠየቅም ቤተ ክርስታያኗ ፈቃድ ሰጥታኛለች ያለ ሲሆን ይህንንም የሚያረጋግጥ ሰነድ በደብራችን አልተገኘም ብለዋል፡፡
አክለውም ድርጅቱ ከተግባሩ የማይመለስ ከሆነ የቤተ ክርስቲያኗ ክብር እንዲከበር ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት እና ከሀገረ ስብከቱ የሕግ ክፍል ጋር በመሆን እርምጃዎችን ለመውሰድ እንገደዳለን ሲሉ ተናግረዋል።
መረጃው፡- በማኅበረ ቅዱሳን ወልድያ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው።
4 comments
በዚህ ዘመን ምን ያልተደፈረ የቤተ ክርስቲያን ንብረት አለ?
እንዲሁ የሳምንት አጀንዳ ከመሆን ውጪ
በጉዳዩ መፍትሄ ይሰጡናል ሕገ ቤተክርስቲያንን ያስከብሩልናል የምንላቸው ሲኖዶሱም ቤተክህነቱም ቄሱም ሰባኪውም .. በመንበራቸው በማንነታቸው በክብራቸው በክህነታቸው አይምጡባቸው እንጂ ለእንዲህ አይነት ክብረ ነክ ለቤተክርስቲያን ጉዳዮች ጉዳያቸውም አይደለም እንዲሁ ነው ምትጮኹት !!
እነሱ እንደሆን የያዙት ፈሊጥና ትልቁ ስራቸው በዓል ሲመጣ በየፊናቸው ሆነው የመግለጫ ጋጋታ ማሰማት ሆኗል
የአባቶቻችን የቤተክርስቲያን አምላክ ይፍረድ!
ለ ዲዛይኑ መክፈል ያለበትን ገንዘብ እንዲከፍል ቢደረግ ባይ ነኝ ።
አይ የናንተ ነገር ክብር ምን እንደሆነ አታውቁም።
በሽቶ አድርጎ ማስተዋወቁ ምን ችግር አለው?
አርዕት አጠቃቀማችው ግን አንዳንዴ ትጨልላላችው😂