banner

የ5 ሚሊዮን ብር ዕድለኛው ገነቱ ታምራት ነው፡፡

ገነቱ ታምራት የተወለደው በከምባታ ዱራሜ ከተማ ነው፡፡ በትምህርቱ በችግር ምክንያት ከስምንተኛ ክፍል ማለፍ አልቻለም፡፡ ትምህርቱን አቋርጦ ሊስትሮ ሆነ፤ ከዚያም እዚያው ዱራሜ ከተማ የጎሚስታ ስራ ጀመረ፡፡ ዱራሜ አልሆንልህ ሲለው ሀዋሳ ገብቶ ጎሚስታ ስራውን ቀጠለ፡፡ ጎሚስታ ስራውን ትቶ ደግሞ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ረዳት ሆነ፡፡ሚስትም አገባ፡፡ ብዙም ሳይቆይ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ የሲኖትራክ ሹፌር ሆነ፡፡ አሁን የአንድ ልጅ አባት ነው፡፡

ከሊስትሮ ስራው ጀምሮ ሎተሪ ያለማቋረጥ የሚቆርጠው ገነቱ በሀዋሳ ከተማ ከስራው አረፍ ብሎ ቡና እየጠጣ የቆረጣት የልዮ ዕድል ሎተሪ የ2ኛ ዕጣ የ5 ሚሊዮን ብር አሸናፊ አድርጋዋለች፡፡
በደረሰው ገንዘብ ምን ለመስራት እንዳቀደ በቃለ መጠይቃችን ጊዜ ስንጠይቀው ቤተሰብ መርዳትና ያቋረጥኩትን ትምህርት መቀጠል አንዱ ትልቁ እቅዴ ነው፡፡ የሲኖትራክ ተሽከርካሪ ገዝቼ በራሴ መኪና መስራት ሌላው ትልቁ እቅዴ ነው ብሏል፡፡

4 comments

Menen M Mesfin February 15, 2025 - 10:43 am

ደስ ይላል ይባርክለት

Reply
Lencho Gerba February 15, 2025 - 10:44 am

5 ሚሊዮን አግኝተህ ትምህርት ቀጥላለው ማለትህ መሃይም መሆንህን ያሳያል በሉልኝ😂

Reply
Na Ti February 15, 2025 - 10:45 am

ትንሽ እቅዶችህ አላነሱም 🥺

Reply
ማህደር የሽወንድ February 15, 2025 - 10:45 am

ንገሩት በልቤ ከብዷል🥰🥰🥰

Reply

Leave a Comment