banner

ይህ መረጃ አሳዛኝም አስተማሪም ስለሆነ በፋስት መረጃ አቅርበነዋል።

ወጣቱ አረብ ሀገር የምትኖረዋን ልጅ በፌስቡክ ይተዋወቃል፣ ፍቅር ጀመሩ የእሱ ፍቅር አላስቀምጥ አላሰራ ብሏት ከስድስት ወር ትውውቅ በኋላ ወደ ሀገር ቤት መጣች።

ወደ ሀገር ቤት መጣች ተቀበላት ቦሌ ወረዳ 12 ቤት ተከራይቶ ገቡ፣ ይህ ሁሉ ሲሆን ቤተሰብ አያውቅም። በሚያሳዝን ሁኔታ በዛው ቀን ለእሱ ብላ የመጣችውን ፍቅረኛውን ገደላት።

ከገደላት በኋላ ሬሳዋን ጠቅልሎ ቤት ውስጥ ካስቀመጠ በኋላ ይዛ የመጣችውን ንብረት ይዞ ጠፋ።

የእሱ አድራሻ እንዳይታወቅ አከራዮቹን «ፋይዳ መታወቂያ ላወጣ ስለሆነ እናንተ ጋር ያለውን መታወቂያ ኮፒ ስጡኝ» ብሎ ተቀብሎ እንደሄደ አከራዮቹ ይናገራሉ።

ከአንድ ሳምንት በኋላ አከራዮቹ ጥሩ ያልሆነ ሽታ በመኖሩ ለፖሊስ አመልክተው በሩ ሲከፈት ሬሳ ቤቱ ውስጥ ተገኘ።

እሱ ብቻ እንደተከራየ የሚያውቁት አከራዮች የሴት ሬሳ ቤት ውስጥ መገኘቱ ዱብ እዳ ነው የሆነባቸው። የተገኘው ሬሳ ለምርመራ ሆስፒታል ከገባ በኋላ ቤቱን የተከራየው ልጅ ሲፈለግ አንድ መንገድ ተገኘ።

የቤት ኪራይ በባንክ አስገብቶ ስለነበር ስልክ ቁጥሩ ተገኝቶ በጂፒኤስ ልጁ እዛው ሰፈር መጠጥ ቤት እየተዝናና ሊያዝ እንደቻለ ለፋስት መረጃ ጉዳዩን ያስረዱ ግለሰቦች ገልጿል።

ከተያዘ በኋላ ያደረገውን ሁሉ በዝርዝር እና በድርጊት በቦታው በመገኘት አሳይቷል።

ጉዳዩን አሳዛኝ የሚያደርገው የልጅቷ ቤተሰቦች ልጃቸው አረብ ሀገር እንዳለች ነው የሚያውቁት። (ይህ መረጃ የደረሰን jan 26 ሲሆን በወቅቱ የልጅቷ ቤተሰብ እየተፈለገ እንደነበር ነው)

10 comments

Ef Rem February 15, 2025 - 7:08 pm

ኧረ ፋስቶች የሰሞኑን መረጃ የሆረር ፊልም ሆነብን እኮ😥 እንዲህ አይነቱ መረጃ ቢታላፍ

Reply
Abby Junior February 15, 2025 - 7:09 pm

ብዙ ነገሩ ግራ ነው

በመጀመሪያ ቀን መግ*ደል ምን አይነት ህሊና ነው?

እቤት ውስጥ ጠቅልሎ ሬሳ አስቀምጦ ለማምለጥ መሞከር ምን አይነት አይምሮ ነው?

ሰው ገ*ድሎ የሚያዝናና ምን አይነት ሰውነት ነው?

የተበዳይ ደም ለፍትህ ይጮሃል 😭

Reply
Tîg Arsenal February 15, 2025 - 7:09 pm

ሰሞኑን እሚወጠው መረጃ ግን ሳስፈራ በጌታ ወይኔ ግን ሰው እደዚህ ጨካኝ ሆኖል እዴ እግዚኦ 😭💔

Reply
Betelhame Mulualem February 15, 2025 - 7:10 pm

ቤተሰብ መከረኛ ነዉ ትመጣለች ብሎ እየጠበቀ

Reply
ቼልሲ ያያ February 15, 2025 - 7:12 pm

ሀርብ ሀገር ያላቹ ሰቶች ግን በሳባቼው ነው ምያሰቡት

Reply
Zeinu Zuber February 15, 2025 - 7:13 pm

fastmerejawoch mendenew merdo negarenet aiselechachum ?

Reply
Dawit Be February 15, 2025 - 7:13 pm

እኛ መስማት ምንፈለገው ጥሩ ፍርድ ተፈርዶ የተፈረደው ፍርድ ሲተገበር ነው። ከዛ ውጭ ሌሎች ከዚህ የባሰ ወንጀል እንዲፈፅሙ ማበረታታት ነው ሚመስለኝ ደሞም ነው።

Reply
Mihireteab Fasil February 15, 2025 - 7:14 pm

ለዚህ ሁሉ ምክንያት የህግ መላላት እንዲሁም የህግ ተርጓሚ እና የህግ አስፈፃሚ አካላት እንዝላልነት ነዉ.

Reply
Abdulkaf Murad February 15, 2025 - 7:15 pm

እንዲ አይነት ነገር ሲመሽ ለምን ፖስት ታደርጋላቹ? እንተኛበት እንጂ😭

Reply
Gibril Abege February 15, 2025 - 7:18 pm

ፈጣሪ ሆይ ምነው የኢትዮጵያን ህዝብ ኧረሳሀው በማዕበል ጥርግርግ አርገን

Reply

Leave a Comment