banner

ዘ ታቦር ትሬዲንግ ወርክ ሾፑን አስመረቀ

#FastMereja I ዘ ታቦር ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች ዋና አከፋፋይ በዛሬው ዕለት የወርክ ሾፕ የምረቃና ጉብኝት መረኃ ግብር በአፐር ናይል ሕንፃ ላይ አካሄዷል።

ዘ ታቦር ትሬዲንግ ላለፉት ዓመታት ለቤት፣ ለተቋማትና ድርጅቶች የዘመኑ ቴክኖሎጂ ያፈራቸውን የግንባታና ዲዛይን ማስዋቢያ ማቴሪያሎችን በማከፋፈል በዘርፉ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን ከሚሰራቸው የንግድ ስራዎች መካከልም
የሀገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነውን የግብርና ምርቶች ወደ ውጭ መላክ፣ የፋብሪካ ግብአት የሚሆኑ ምርቶችን ማስመጣት እና የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎችን እያከፋፈ የሚገኝ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ከነዚህ በተጨማሪ በዛሬው እለት ከ30 በላይ የኮንስትራክሽን ፊኒሽንግ እቃዎችን ማከፋፈል መጀመሩን ያሳወቀ ሲሆን ከነዚህም መካከል የወለል ምንጣፍ (SPC) ሙሉ በሙሉ ሴራሚክን የሚተካ በሀገራችን በኢትዮጵያ የሚመረት ለሴራሚክና ለወለል ምንጣፍ የሚሆኑ፣ ለጣራና ግድግዳ የሚያገለግል Wall Board & Foam Board እና Live ቦርድ
እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በዚህ መረኃ ግብር ልዩ ልዩ የግንባታ ማስዋቢያ የኮንስትራከሽን ማቴሪያሎች በአይነትና በጥራት በልዩ ቅናሽ ለገበያ የቀረቡ ሲሆን የግንባታ ማስዋቢያ ማቴሪያሎች የምርት ሂደትና ስለሚሰጡት አገልግሎት በባለሙያ ገለፃ ተደርጓል።

#ቢዝነስ





Leave a Comment