0
#FastMereja I የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ከተመሰረተችበት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 20 አመታት ወንጌል የመስበክ እና የማስተማር ተልዕኮ አንግባ የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች፣ የቆየች እና እያገለገለች ያለች ቤተክርስቲያን እንደሆነች ዛሬ በአዲስ አበባ ሳሮ ማርያ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ተገልጿል።
ቤተክርስቲያኒቱ ቀድሞ በተከራየችበት በጎተራ የእህል ንግድ ድርጅት ግቢ ውስጥ ላለፉት 18 አመታት የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች እንደቆየች የተገለጸ ሲሆን፣ አሁን የራሷን የማምለኪያ አዳራሽ ገንብታ የምስጋና ኮንፈረንስና የአዳራሸ ምረቃ ፕሮግራም ከመጋቢት 1-7/2017 ዓ.ም ታላላቅ አገልጋዮች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አባቶች በተገኙበት ለማስመረቅ ዝግጅት መጠናቀቁ ነው የተነገረው።
አሁን የተገነባው የማምለኪያ አዳራሽ ጎተራ ማሳለጫ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ አጠገብ ሲሆን የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ኑና የረዳንን እግዚአብሔርን አብረን እናመስግን በማለት ጥሪዋን አቅርባለች።
#ማህበራዊ





2 comments
HBD!
መልካም ልደት ለሰላም 🎊🍬🍬