#FastMereja I የሰው ልጅ ለገደላቸው እንስሳት ሁሉ በህግ ቢጠየቅ እስር ቤቶች በሰዎች ይሞሉ ነበር፡፡ ከወደ ሱዳን ያጋጠመው ክስተት ግን ለየት ያለ ነው፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በጎረቤት ሀገር ሱዳን ምስራቃዊ የሀገሪቱ አካባቢ በምትገኘው ሩምቤክ ተብላ በምትጠራ አካባቢ አንድ ሙክት በግ አንዲት አዛውንት ላይ ባደረሰው ጉዳት ከቀናት ህመም በኋላ ህይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል፡፡
አዛውንቷ በበጉ ግጭት ምክንያት የጎድን እና ዳሌ አጥንታቸው ተጎድቷል የተባለ ሲሆን በህክምና ላይ እያሉ ህይወታቸው አልፏል፡፡
በሀገሪቱ የባህላዊ አስተዳድር ወይም ሽምግልና መሰረት የበጉ ባለቤት ሀላፊነት እንዲወስድ ተደርጓል የተባለ ሲሆን ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል እንደተስማማ ተገልጿል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ግን በጉ አዛውንቷን ሲገጭ ባዩ የአይን እማኞች አማካኝነት የሶስት ዓመት እስር የተላለፈበት ሲሆን ቅጣቱን በወታደራዊ ካምፕ ይጨርሳል መባሉን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በግጭቱ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈው አዛውንት የበጉ ባለቤት አምስት ላሞችን በካሳ መልክ ለመክፈል መስማማቱም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ወንጀለኛ ነው የተባለው ይህ በግም የሶት ዓመት የእስር ጊዜውን ሲጨርስ ለተጎጂ ቤተሰቦች ተላፎ ይሰጣልም ተብሏል፡፡
Via: ዐል ዐይን
#ችሎት

9 comments
Ke egna ager meslogn sef maletie
ለምን ለቅሶ ላይ አርዶ አይበሉትም?
hoooo endim ale sew sewn sigels sint deres?
ኡፍ
እነሆ በመጨረሻው ዘመን አዛውንት አዛውንቶች ላይ ይነሳል😎😅
በጉ ለበጎች መብት ጥሰት በሙሉ ልብ ስታገል የቆየ ነዉ🙄
ብገ “ ድልም ለአዛዉንቱ አስቦ ነዉ🥺
ፍትህ ለበጉ😌
ይህ ለወታደራዊ ካምፑ ንቀት ነው፣ ወታደራዊ ካምፕ ጀግኖች ለሀገር መስዋእትነት የሚከፍሉ ውድ ወታደሮች የሚሰለጥኑበትና የሚኖሩበት እንጂ የበግ በረት አይደለም።
ይሄ ውስጡ ፍየል ነው 😐
የማይመሰል ነገር ለምን ታወራላችው