#FastMereja I ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ550ሺህ ቶን በላይ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የውኃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ም/ቢሮ ኃላፊ እና የማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሔለን ዮሐንስ ገልፁ።
በጋሞ ዞን፣ በወላይታ ዞን እና በቡርጂ ዞን ላይ የድንጋይ ከስል ማዕድን ምርት ስራ የተጀመረባችው አከባቢዎች ሲሆን በጋሞ ዞን እና ኮሬ ዞን ላይ የካርትዝ ማእድን ምርት፣ በደቡብ ኦሞ ዞን የግራናይት ማእድን እና ኮንሶ ዞን ላይ በከፊል የከበሩ (አካማሪንና ኤመራልድ) ማዕድናት ምርት ስራ መጀመራቸውን ወ/ሮ ሔለን ገልጿል።
በጋሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ 15 ኩባንያዎች የድንጋይ ከሰል ማዕድን ምርት ስራ ላይ የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ኩባንያዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ550ሺህ ቶን በላይ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ለማዕከላዊ ገበያ አቅርበዋል፡፡ በዚህም ወርዳው ከዘርፉ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በቀጥታ አግኝቷል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስከ 2017 ሁለተኛ ሩብ አመት ድርስ የምርመራ ፈቃድ ለ5 ድርጅቶች የሰጠ ሲሆን በኢፌዲሪ ማዕድን ሚኒስቴር በኩል ደግሞ 2 የምርምራ ፈቃድ (ካፊ ሚኒራልስ እና ዮ ሆልድንግ የተስኙ ድርጅቶች) ተስጥታል ብለዋል።
ወ/ሮ ሔለን አያይዘውም በፌደራል እና በክልሉ በድምሩ 211 ኩባንያዎች ፈቃድ ተሰጥቷል። እነርሱም (የአነሰተኛ ኢንዱስትሪ (209) ፣ የከፍተኛ ኮንስትራክሽን (1) እንዲሁም የልዩ አነስተኛ የጌጣጌጥ ማዕድናት (1) የምርት ፈቃድ የወሰዱ ኩባንያዎች ናቸው። እነዚህ ኩባንያዎች የማዕድን ምርት ጀምረው በሀገራችን ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብ ጀምረዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በዘርፉ ውስጥ እያንዳንዱ አልሚ ከ100-500 የሚሆኑ የአካባቢውን ወጣቶች በመቅጠርና በስራቸው በማደራጀት (በለቀማ፣ በሸራ አሳሪነት፣ በተራ አስከባሪነት፣ በመኪና አቅራቢነትና በመሳሰሉት) ስራ ላይ በማሳተፍ ከ30 በላይ ማህበራት እንዲሰማሩ የተደረገና (3,000) በላይ ሰራ አጥ ወጣቶች ስራ እድል መፍጠር አስችሏል ብለዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸውን የኤክስፖርት ማዕድናት፣ የድንጋይ ከሰልና ሌሎች የጌጣጌጥ ማዕድናት በማልማት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተውን ድርሻ ከፍ ለማድረግና በዘርፉ ለወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ክልሉ ላይ በተለያዩ በህገ ወጥ ድርጊት በተያያዘ ሀሰተኛ ሰነድ የተገኘባችው ድርጅቶች ላይ እርምጃ የተወሰድ ሲሆን በተጨማሪም በግለሰቦች ፍላጎት ብቻ ለረጅም ጊዜ ታጥረው የነበሩ የማዕድን መገኛ ቦታዎች ለአልሚዎች እና ማልማት ለሚችሉ አካባቢው ማህበረስብ እንዲተላለፉ ተደርጋል በማለት ወ/ሮ ሔለን ዮሐንስ ም/ቢሮ ኃላፊ እና የማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ ኃላፊ አስረድተዋል፡፡

6 comments
ለምንድነው የተቆጣችው ታዲያ 🤔
በእግዚአብሔር ለወንድ ሥራ ካለ ፈልጉልኝ አባቴ አርፏል እኔ ተመርቀ ሥራ አጣው የቀን ሥራ እሰራ ነበር ግን ሥራ አንዴ ይኖራል አንዴ ደግሞ ይጠፋል ተቸገርኩ እናቴ ነበረች ፅዳት እየሰራች የሚታበላን አሁን ግን እሷም ትንሽ አሟት ተኝታለች በጣም ከፍቶኛል ቸግሮኛል የትኛውንም ሥራ እሰራለው
የምትችሉ አስቤዛ መግዣም አግዙኝ 🙏 😭
ትራምፕ እንዳይሰማ!😢
የተጨማለቀ ሰክተር
😡 this emoji had a face
የፋና ዶክመንተሪ “የማዕድን ቁማር” ለህዝብ እይታ እንዳይቀርብ ያስከለከሉት ለምንድነው ?? እሱ ይቅረብና የእነዚህን ሪፖርት እንሰማለን ።