banner

ሸማ ኢትዮ ደቡብ ሱዳን የተሰኘው መርሃ ግብር ተከፈተ

#FastMereja I ሸማ ኢትዮ ደቡብ ሱዳን የተሰኘው 69ኛው የስዕል፣ የፋሽን እና የእውቅና መርሃ ግብር ዛሬ የካቲት 29/2017 ዓም በአዲስ አበባ ሳፋየር አዲስ ሆቴል ተከፈተ።

በሰዓሊ ራስ በረከት አንዳርጌ የተሳሉ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳንን ግኑኝነት የሚያሳዩ ስዕሎች እንዲሁም ማርች 8 በማስመልከት ክብር ለእናቶች፣ ጥበብ ለሴቶች የተሰኘ የስዕል አውድ ርዕይ ለእይታ ቀርቧል።

የሴቶችን ህይወት ለመለወጥ እና በአርአያነት የሚጠቀሱ ኢትዮጵያውያን እና ደቡብ ሱዳናዊያን በመድረኩ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቅበትን ጥበብ መነሻ በማድረግ ልዩ የስዕል አውደ ርዕይ የፋሽን ሾው እና ኤግዚብሽኑ እስከ መጋቢት 8/2017 ዓም ድረስ የሚቆይ ይሆናል።

#ማህበራዊ





1 comment

ቢኒ የእናቱ ልጅ March 8, 2025 - 2:07 pm

በእግዚአብሔር ለወንድ ሥራ ካለ ፈልጉልኝ አባቴ አርፏል እኔ ተመርቀ ሥራ አጣው የቀን ሥራ እሰራ ነበር ግን ሥራ አንዴ ይኖራል አንዴ ደግሞ ይጠፋል ተቸገርኩ እናቴ ነበረች ፅዳት እየሰራች የሚታበላን አሁን ግን እሷም ትንሽ አሟት ተኝታለች በጣም ከፍቶኛል ቸግሮኛል የትኛውንም ሥራ እሰራለው
የምትችሉ አስቤዛ መግዣም አግዙኝ 🙏 😭

Reply

Leave a Comment