#FastMereja I ቢክ እስኪብርቶ በኢትዮጲያ ከንጉሱ ጊዜ ጀምሮ በዋናነት አገልግሎት ላይ ውሎ የነበረ ሲሆን አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርም ከሃያ አመታት በፊት ጀምሮ ቢክ እስኪብርቶን በብቸኛ አስመጪነትና አከፋፋይነት በኢትዮጲያ ውስጥ ለገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
ምርቱንም ያስመጣ የነበረው ከኬንያ አገር ለረዢም ጊዜ ሃኮ ኢንደስትሪስ ከሚባል ኩባንያ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከቢክ ኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ከሚባለው ተቋም እንደሆነ ተገልጻል።
አልሳም ቢክ እስኪብሮቶን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ዛሬ የካቲት 29/2017 ዓም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ከኢስት አፍሪካ ሊሚትድ ጋር የአጋርነት ስምምነት አድርጓል።
አልሳም ከማምረቱ በተጨማሪ የምርቱ ስርጭትም ለምስራቅ አፍሪካ አገሮች ኢትዮጲያን ጨምሮ ለጅቡቲ፣ ለሶማሊያና ለኤርትራ የሚያከፋፍል ይሆናል።
የቢክ እስክብርቶ በኢትዮጲያ መመረት በአከባቢው ካለው የገበያ ስፋት አንፃር ለአገራችን የቴክኖሎጂ ሽግግር ይፈጥራል፣ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል፣ ለዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
በቀጣይ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱን ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የተገለጸው።
አልሳም ኃላ/የተ/የግል ማህበር ከተመሰረተ 25 ዓመታት ያለፉት ሲሆን በአስመጪነት፣ በላኪነት፣ በአገር ውስጥ ንግድ፣ በሪል እስቴትና በማኑፋክቸሪንግ የሥራ ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል።
#ቢዝነስ





7 comments
ክፍት የስራ ቦታ
ስራ….ዜና ለዮቱብ
ቋንቋ ኦሮምኛ አማርኛ
የስራ ቦታ ADAMA
ደምዝ በስምምነት
0944161123
ላካ ከኬንያ ነበር የሚመጣው
ደስ ይላል
በጣም ተጨንቀን ነበረ ባካቹ
ስራ በሌለበት አገር እስኪሪቢቶ 😂
የሚፃፍ ነገር የለን
በዚህ ቢል ግራሀም በዚያ ደግሞ ቢክ እስክሪብቶ የሰሞኑ አጀንዳ ልትሆንብን ነው።
ሰሞኑን ሊመረት ነው ና አመረተች በዛ 😜😜😜😜 Next 👴