#FastMereja l አዋሽ ባንክ ከመደበኛው የባንክ አገልግሎት ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በዛሬው እለትም ቅዳሜ መጋቢት 06 ቀን 2017 ዓ.ም 1446ኛውን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ በሸራተን አዲስ ሆቴል የኢፍጣር መርኃ ግብር አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ አዋሽ ባንክ
📌 ለአወልያ እርዳታና ልማት ድርጅት ት/ቤት ማስፋፊያ 5 ሚሊዮን ብር
📌 ለታላቁ አነዋር መስጂድ የከርስ ምድር ውሃ ቁፋሮ የሚውል 7 ሚሊዮን ብር
📌 በኢትዮ ጥበብ ሆስፒታል 20 ሰው የአንድ አመት ኩላሊት እጥበት የሚውል 6.9 ሚሊዮን ብር
📌 በአሜን ጀነራል ሆስፒታል ለ12 ሰዎች ኩላሊት እጥበት 4.6 ሚሊዮን ብር
በአጠቃላይ 23.5 ሚሊዮን ብር ባንኩ ድጋፍ አድርጓል።
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝቶ እንደተናገሩት፣ የህብረተሰባችንን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባንኩ ላለፉት 30 ዓመታት ዘርፈ ብዙ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸ፣ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ዘመናዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ከደንበኞቹ ጋር ዘመናትን መሻገሩን ገልጸዋል።
አዋሽ ባንክ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ጥራቱንና የሸሪዓ መርህን በተከተለ መልኩ አዋሽ ባንክ ኢኸላስ’ በመባል የተሰየመው የባንካችን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከሰባት ዓመት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን መሰረታዊ መርህን በመከተል ንፁህና የሸሪዓ ህጉን በማክበር በታማኝነት እና በቅንነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።




